በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት 9.3 ሚሊዮን የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች የከፋ ጉዳት ላይ ናቸው ተባለ፡፡ በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት 9.3 ሚሊዮ…

በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት 9.3 ሚሊዮን የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች የከፋ ጉዳት ላይ ናቸው ተባለ፡፡

በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት 9.3 ሚሊዮን የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ የምግብ እና የመድሃኒት ችግር መጋለጣቸውን የክልሉ የአደጋ መከላከል ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት 9.3 ሚሊዮን የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ የምግብ እና የመድሃኒት ችግር የተጋለጡ እንደሆነ እና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን የክልሉ የአደጋ መከላከል ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ እያሱ መስፍን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አቶ እያሱ ጨምረውም 2.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ እስካሁን ተፈናቅለው ወደ ቀያቸው ያልተመለሱት መሆናቸውን ነው የነገሩን፡፡

ለተጎጂዎቹ በየወሩ 1.2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆን የምግብ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነም አንስተው ነገር ግን አጠቃላይ አሁንም በክልሉ 11.6 ሚሊዮን የሚሆኑት የምግብ እና የመልሶ ማቃቋም ስራ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply