በአማራ ክልል በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 14 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

በአማራ ክልል በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 14 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በአማራ ክልል ዝናብ አጠር እና ደረቃማ አካባቢዎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች እደሚገነቡ ተገለፀ፡፡
በክልሉ በመካከለኛ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ያለውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሳደግ ያስችላል የተባለለት ይህ ፕሮጀክት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በሰሜን ወሎ፣ ማዕካላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሽዋ ዞኖች እንደሚገነባም ታውቋል፡፡
የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆኑት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስ ከተማ እና በሰሜን ወሎ ዞን ሰኞ ገበያ የሚገነቡት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡
የግንባታ ውሉ የፊርማ ሥነ ሥርዓትም በፕሮጀክቱ አስፈፃሚ የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ እና በሚገነባው የጢስ እሳት ኮንስትራክሽን ድርጅት መካከል ተካሂዷል፡፡
14ቱ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች በአየር ንብረት አይበገሬነት የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ፕሮግራም የሚከናወኑ ናቸው ያሉት የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌው ግንባታቸው በመጨዎቹ ሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መመደቡንም የቢሮዉ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ግንባታ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ፣ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ተገኝተዋል፡፡
አብመድ እነደዘገበው ለፕሮጀክቶቹ ተፈፃሚነት የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የውኃ ልማት ኮሚሽን እና የአማራ ክልል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ በጋራ እንደሚሰሩም ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአማራ ክልል በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 14 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply