በአማራ ክልል በ147 ሴቶች ላይ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት መፈፀሙን ክልሉ አስታወቀ

በአማራ ክልል የህወሃት ኃይሎች ተቆጣጥረው በቆዩባቸው አካባቢዎች ብዙ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈፀማቸውን የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ባካሄደው መጠነኛ የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን ገለፀ።

የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አስናቁ ድረስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የህወሃት ኃይሎች በአማራ ክልል በቆዩባቸው  አንዳንድ አካባቢዎች ቢሮው ባደረገው መጠነኛ የዳሰሳ ጥናት 147 ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

የዳሰሳ ጥናቱ በቅርቡ የተለቀቁ አካባቢዎችን የማይጨምር መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ አስናቁ እነዚህ አካባቢዎች ሰጨመሩ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ገልፀዋል። 

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply