በአማራ ክልል ባለው ፀጥታ ችግር ምክንያት በትራንስፖርት ዘርፍ ቁጥጥር ማድረግ አለመቻሉን የክልሉ የትራንስፖርትና ሎጂሲቲክ ባለስልጣን አስታወቀ።በአማራ ክልል ከለፈው አመት ሃምሌ 24 ቀ…

በአማራ ክልል ባለው ፀጥታ ችግር ምክንያት በትራንስፖርት ዘርፍ ቁጥጥር ማድረግ አለመቻሉን የክልሉ የትራንስፖርትና ሎጂሲቲክ ባለስልጣን አስታወቀ።

በአማራ ክልል ከለፈው አመት ሃምሌ 24 ቀን ጀምሮ በትራንስፖርት ዘርፍ ቁጥጥር ማድረግ አለመቻሉን የአማራ ክልል የትራንስፖርትና ሎጂሲቲክ ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ዘውዱ ማለደ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

ክልሉ በኮማንድ ፖስት ስር መሆኑ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ባለሙያዎች ከሰላም አስከባሪዎች ጋር በቅንጅት ወጥተዉ ተናበው ለመስራትም አልተቻለም ነው ያሉት።

በዚህም በክልሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ውስንነት እንዲሁም የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ያልተገባ የታሪፍ ጭማሪ ተፈጥሯል ተብሏል ።

ባለስልጣኑ ተንቀሳቅሶ ለመቆጣጠር የሰላሙ ሁኔታ በትራፊክ ተቆጣጣሪ አካላት ላይ ችግር በመሆኑ እርምጃ መውሰድ አልተቻለም ብለዋል።

አቶ ዘውዱ ከለፈው አመት ከሃምሌ 24 ቀን አንስቶ እከዛሬዋ ቀን ድረስ በመናሃሪያ ካልሆነ ወደ መንገድ ወጥተው ለመቆጣጠርና እርምጃ ለመውሰድ ያለው የሰላም ሁኔታ አዳጋች ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በክልሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በሲሚንቶ ፣በብረታ ብረትና ሌሎች ግብዓቶች እጥረት ግንባታቸው በተፈለገው ልክ እየሄደ አደለም ብለዋል ።

በመጨረሻም ክልሉ ባለው የሰላም እና ፀጥታ ችግር ምክንያት አሁን ላይ በቱሪዝ፣በኢንቨስትመንት ፣በኮንስትራክሽን ፣በትራንስፖርት ፣ እንዲሁም በትምህርት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትም ገልፀዋል ።

በልዑል ወልዴ

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply