
በአማራ ክልል በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች ሕግ ማስከበር ያሉትን እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ቀናት በተከሰቱ ግጭቶች በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ። በምሥራቅና በምዕራብ ጎጃም በሰሜን ወሎ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት ሰው ሕይወት መጥፋቱን ተነግሯል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተረጋጋና ዘላቂ ልማት የሚከናወንበትና ዜጎች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ክልል እንዲሆን ጠንካራ የሕግ ማስከበር ተግባራር እየተከናወነ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።
Source: Link to the Post