በአማራ ክልል ” ኢትዮጵያ ታምርት” የኢንቨስትመንት ንቅናቄ መድረክ በባሕርዳር እየተካሄደ ይገኛል ።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄው ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ብልፅግና ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደተገኙ ታውቋል።
የንቅናቄ መድረኩ በክልሉ ያለውን ፀጋ ለአልሚ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ ትልቅ ድርሻ አለው ተብሏል።
በክልሉ ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶች እየገጠሟቸው ባሉ ችግሮች ዙሪያም ውይይት እንደሚደረግም ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሰምቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።