You are currently viewing በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው “ህግ ማስከበር” በሚል የሚደረገው አፈና  የሚመራው  በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ግሩፕ በሚደረግ የፁሁፍ ውይይት መሆኑን የአሻራ የሳይቨር  አጥኝ ቡድን ደርሶበ…

በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው “ህግ ማስከበር” በሚል የሚደረገው አፈና የሚመራው በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ግሩፕ በሚደረግ የፁሁፍ ውይይት መሆኑን የአሻራ የሳይቨር አጥኝ ቡድን ደርሶበ…

በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው “ህግ ማስከበር” በሚል የሚደረገው አፈና የሚመራው በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ግሩፕ በሚደረግ የፁሁፍ ውይይት መሆኑን የአሻራ የሳይቨር አጥኝ ቡድን ደርሶበታል። የአማራ ክልል የሰላም እና ደህንነት ምክትል ቢሮ ሀላፊ በሆነው በመንገሻ አውራሪስ የተከፈተውና በበላይነት የሚመራው የዋትስአፕ እና የቴሌግራም ግሩብ ሙሉ ውይይትም እጃችን ላይ ገብቷል። አሻራ እንደተመለከተው አቶ መንገሻ አውራሪስ ከፀጥታ ሀይሎች 15 ሰዎችን ከግሩቡ ያባረሩ ሲሆን፣ በምትኩ ሌሎች ታማኝ የሚባሉትን አስገብተዋል። የእነዚህ ግሩብ አባላት እከሌ ይታሰር እያሉ በፅሁፍ እስከ ምክንያቱ ያብራራሉ። በዚህ መሰረት ካለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ መንገሻ አውራሪስ በደህንነት የተገኘ መረጃ ነው ብሎ በግምት ሪፓርት ያደርጋል። ሪፓርቱን ተከትሎ በደስየ ደጀን የሚመራው ልዩ ኃይል እና አድማ ብተና የኦፕሬሽን ዘርፍ፣ ከፌዴራል ሀይልና መከላከያ ጋር ሆኖ አፈና ያደርጋል። ባልተጣራ መረጃ እስሩ፣ (የምወዳትን ሴት ነጥቆኛል ተብሎ የታፈነም አለ)፣ በቂም በቀል፣ በጥቅም ቅራኔ የተጀመረው አፈና ብልፅግና ሳይሳካለት የቀረውም ምክንያት የለሽ በመሆኑ እንደሆነ አሻራ ማረጋገጥ ችሏል። የአማራ ክልል የፀጥታ ቡድን የዋትስአፕ እና የቴሌግራም ቡድን እንደመረመረው ለክልሉ ሰላም ሳይሆን ለየራሳቸው የሚሰሩ ሆዳሞች የበዙበት እንደሆነ አሻራ ታዝቧል። በዚህ የሳይቨር ቡድንተኛ መረጃ አሰባሰብ የሚመራው ቡድን ማን ስለማን ምን እንዳለ ለታሪክም ሆነ ለማህበረሰብ ሞራል ጠቃሚ ባለመሆኑ በአደባባይ ለማውጣት እንቸገራለን። ለማንኛውም እነ መንገሻ አውራሪስ አደብ ግዙ፣ ይሄ ቀን ያልፋል። ትዝብቱ እና የወደፊት ተጠያቂነቱ እንዳለ ሆኖ። የነ ይልቃል ከፋለ ቡድን በውሸት መረጃ ተደናቁራችሁ ክልሉን አታምሱት። አሻራ ሚዲያ አምስተርዳም

Source: Link to the Post

Leave a Reply