
በአማራ ክልል ከ4ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የጸጥታ ቢሮው ዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከሰሞኑ መንግሥት ያካሄደውን “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” ተከትሎ መሆኑን አመልክቷል። በቁጥጥር ስር የዋሉት አጠቃላይ ተጠርጣሪዎች ብዛት 4 ሺህ 552 እንደሆነና ከእነዚህ ውስጥ 210 የሚሆኑት በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ምርመራ ተጣርቶባቸው የተከሰሱና በሕግ ጥላ ስር ማድረግ ሳይቻል የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል።
Source: Link to the Post