በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የጻግብጂ እና አበርገሌ ወረዳዎች አሁንም በአገው ሸንጎ እና በህወሀት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መሆናቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2…

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የጻግብጂ እና አበርገሌ ወረዳዎች አሁንም በአገው ሸንጎ እና በህወሀት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መሆናቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል ዋግኽምራን በተመለከተ ወንዴ ብርሃኑ ካባው (Wonde Berhanu Kabaw) የተባለ በዋግኽምራ ጉዳይ በመጻፍ የሚታወቅ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የሚከተለውን መረጃ አጋርቷል:_ 1) አሁንም ድረስ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ሁለት ወረዳዎች (ጻግብጂና አብርገሌ) በአገው ሸንጎና ህወሀት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ናቸው። 2) ከፕሪቶሪያው የመንግስትና ህወሀት እርቅ በኋላ ብቻ ከሁለቱ ወረዳዎች ከ5,000 በላይ ህዝብ ከሁለቱ ወረዳዎች ተፈናቅሎ ወደ መዲናዋ ሰቆጣ የገባ ሲሆን ባሁኑ ሰዓት 67,000+ ተፈናቃይ ያለ በቂ ምግብና መጠለያ ሰቆጣ ተቀምጧል። 3) ከተፈናቃዮቹ ውስጥ ከ3,000 በላይ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው። 4) አባታችን አቡነ በርናባስ (የካናዳና ዋግ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ) የአገው ሸንጎና የህወሀት ታጣቂዎችን ወደ እርቅ እንዲመጡና ህዝቡ ወደቀየው እንዲመለስ ለማሸማገል ህይወታቸውን አስይዘው ወደ ተያዙት ወረዳዎች አምርተዋል። 5) ተፈናቃዮቹ ለወራት ምግብ እየቀረበላቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply