በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማር ስራውን ለመጀመር በሽህ የሚቆጠሩ ተመራቂ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም…

በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማር ስራውን ለመጀመር በሽህ የሚቆጠሩ ተመራቂ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም…

በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማር ስራውን ለመጀመር በሽህ የሚቆጠሩ ተመራቂ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል የሚገኙ አምስት ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማር ስራውን ለመጀመር 15 ሺህ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እየተቀበሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ተማሪዎችን እየተቀበሉ ያሉት ባህር ዳር፣ ወሎ፣ ወልዲያ፣ ደብረ ብርሃንና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ስለመሆናቸው ኢትዮ መረጃ ኒውስ ዘግቧል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲም ከዚህ ቀደም የ2012 ዓ.ም መደበኛ ተመራቂ ከሆኑት ተማሪዎች በተጨማሪ የ4ኛ ዓመት መደበኛ ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ፣ የ5ኛ ዓመት የክረምት ኤሌክትሮ መካኒካል፣ የ4ኛ እና የ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎችን እንዲሁም የ3ኛ ዓመት የአኔስቴዥያ ተማሪዎችን ቀደም ሲል በማስታወቂያው መሰረት ከትናንት ታህሳስ 1 ቀን ጀምሮ ተቀብሎ እያስተናገደ መሆኑ ተገልጧል። ከታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ስራቸውን እንደሚጀምሩና የማካካሻ ትምህርቱን በ45 ቀን ውስጥ በማጠናቀቅ ተማሪዎቹን እንደሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎቹ አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply