“በአማራ ክልል የማር ሀብት ልማትን በማስፋት የሌማት ትሩፋትን ለማሳካት እየተሰራ ነው”፡- የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ጽፈት ቤትበክልሉ በበጀት ዓመቱ 22 ሺህ 54 ቶን ማር ለማምረት ታቅ…

“በአማራ ክልል የማር ሀብት ልማትን በማስፋት የሌማት ትሩፋትን ለማሳካት እየተሰራ ነው”፡- የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ጽፈት ቤት

በክልሉ በበጀት ዓመቱ 22 ሺህ 54 ቶን ማር ለማምረት ታቅዶ በተከናወኑ ስራዎች ባለፉት አምስት ወራት ከ13 ሺህ 400 ቶን በላይ ማር መመረቱ ለሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬት መሰረት መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

ክልሉ የተለያየ የአየር ንብረትና ስነ-ምህዳር ያለው በመሆኑ ለንብ ማነብ ስራ የተመቸ መሆኑን በጽህፈት ቤቱ የንብና ሃር ልማት ባለሙያ አቶ ሞሀመድ ጌታሁን ገልጸዋል ።

በክልሉ በባህላዊ፣ በዘመናዊና በሽግግር ቀፎዎች 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የንብ መንጋ እንደሚገኝም ባለሙያው ጠቅሰዋል።

በንብ ማነብ ሥራው 482 ሺህ 491 ሰዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ለእነዚህም በየደረጃው የስልጠናና የግብአት ድጋፍ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በክልሉ የማር ሃብት ልማትን በማስፋፋት አገራዊው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብርን ለማሳካት እንደሚሰራም አቶ ሞሀመድ አስረድተዋል።

“ለዚህም በክልሉ ለንብ ማነብ ምቹ በሆኑ 50 ወረዳዎች 500 ሞዴል መንደሮችን በመመስረት 10 ሺህ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ የቴክኒክና የግብአት ድጋፍ ይደረጋል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply