በአማራ ክልል የተደራጀ የዳታ ቤዝ አያያዝ ስርዓትን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

በአማራ ክልል የተደራጀ የዳታ ቤዝ አያያዝ ስርዓትን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ለዞን አመራርና አባላት የተቀናጀና የተደራጀ የዳታ ቤዝ አያያዝ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ሀላፊ አቶ መስፍን አበጀ የስልጠናው ዋና ዓላማ የተደራጀና የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ አሰራርን ለመዘርጋት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህም ፈጣን፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መረጃን ለመያዝና ለመስጠት አመቺ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ መስፍን ስልጠናውን በተገቢው መንገድ መውሰድና በብቃት መፈፀም እንደሚገባ ለሰልጣኞች አሳስበዋል።

ስልጠናው በስድስት የመረጃ ቋቶች ላይ ተመስርቶ ነው እየተሰጠ ያለው፡፡

በክልሉ በተለይም ከዞን እስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት ያለውን የመረጃ አያያዝ ችግር እንደሚፈታ ታምኖበታል፡፡

ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በመዘርጋት ቀልጣፋ ስራ ለመስራት አመቺ እንዲሆን ታስቦ ነውም ብለዋል።

ስልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ከአማራ ብልጽግና ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአማራ ክልል የተደራጀ የዳታ ቤዝ አያያዝ ስርዓትን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply