በአማራ ክልል የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አይደለም ሲል የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት መግለጫ ሰጠ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 16/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙ…

በአማራ ክልል የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አይደለም ሲል የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት መግለጫ ሰጠ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 16/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዲዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በክልሉ በማህበራዊ ሚዲያ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊ ያልሆነና ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ዜጎችን ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርግ ነው ብለዋል። የገጠመን ችግር ሰልፍ በማድረግ ብቻ የምንፈታው አይደለም ፤ ሰልፍ በማድረግ ችግሩ የሚፈታ ቢሆን የክልሉ መንግስት ሰልፉን መምራት ይችል ነበር ብለዋል። የክልሉ ህዝብ ያጋጠመውን የተፈጥሮ አደጋን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት ሰልፍ መጥራት የአማራ ክልልን መረጋጋት ለማይፈልጉ ሀይሎች ዱላ እንደማቀበል ይቆጠራል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ጸረ ሰላም ኃይሎች በሰልፍ አሳበው ግርግር ለመፍጠርና ዜጎችን ለማጋጨት እንዲሁም ክልሉን የትርምስ ማዕከል እንዲሆን ለማድረግ አልመው እየሰሩ በመሆናቸውን የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አለመሆኑን ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ የክልሉ መንግስት ለሰልፋ እውቅና ያልሰጠ በመሆኑ የክልላችን ህዝቦች በማህበራዊ ሚዲያ የተጠራው ሰልፍ ትክክለኛ አለመሆኑን አውቃችሁ መደበኛ የእለት ከእለት ስራችሁን እንድታከናውኑ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል። ይህንን ተላልፎ ሰልፍ የሚወጣ አካል ካለ ግን የጸጥታ አካላት፤ ፓሊስና ሚሊሻ ስርዓት እንዲያስይዙ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply