በአማራ ክልል የትኛውም አካባቢሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የተጀመረውንህግ የማስከበር…

በአማራ ክልል የትኛውም አካባቢ
ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ
ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የተጀመረውን
ህግ የማስከበር ስራ በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት
ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅሩ ከሰላም ወዳዱ ሕዝብ ጋር
ኾኖ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ሕገወጥ ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ኾነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ
ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የገለጸው ቢሮው፤ በዚህ ድርጊት ላይ
በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት ላይ እንዲሁም
በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ በሚደረጉ
ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን የሕግ የማስከበር እርምጃ
የሚወስድ መኾኑን አስታውቋል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው
መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል:-

የአማራ ክልል ጸጥታ ምክር ቤት የክልሉን የሰላምና እና ደኅንነት
ሁኔታ በጥልቀት ከገመገመ በኋላ የአሸባሪው ትህነግ ወረራ
ስጋትን ለመመከት ዝግጅት ማድረግ እና የክልሉን አንድነት
የሚሸረሽሩ ሕገወጥ ተግባራትን ማረም አስፈላጊ መኾኑን መወሰኑ
ይታወሳል።

ሕግ የማስከበር ሥራው ዋና ዓላማ ሊቃጣ የሚችልን የአሸባሪው
ትህነግ ድጋሚ ወረራ ለመቀልበስ፣ ለክልላችን ሕዝቦች ሰላም እና
ደኅንነት ዋስትና ለመስጠት እንዲሁም የሚታየውን ሕገ ወጥነት
መልክ በማስያዝ ሕዝቡ እየጠየቀ ያለውን የልማት እና መልካም
አሥተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ዓላማ ያደረገ እንደኾነ የክልላችን
ርእሰ መሥተዳድር ለሕዝባችን መግለጻቸው ይታወሳል።

ካለፉት ቀናት ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ሕግ የማስከበር
ሥራ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ግጭት እጃቸውን ለሕግ
እንዲሰጡ የማድረግ እንዲሁም እጃቸውን በሰላም ለሕግ
ለመስጠት ፈቃደኛ ያልኾኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የመቀነስን ሥራ
በመሥራት በሰላም ወዳዱ ሕዝባችን አጋርነት ሕግ የማስከበር
ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

ይህ ሕግ የማስከር ሥራ ለሕዝባችን ሰላም እና ደኅንነት
ለክልላችን እና ሀገራችን የስላም ዋስትናን ዓላማ በማድረግ
እየተከናወነ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከዋና ጠላቶችችን ጋር በማበር
ክልላችንን እና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሠሩ አንዳንድ
የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች እና ግለሰቦች በአንዳንድ
የክልላችን አካባቢዎች ሰልፍ መጥራት እና ለሰላም ማስከብር
ሥራው እንቅፋት የኾኑ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
ነገር ግን በክልላችን የትኛውም አካባቢ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም
ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ የለም።

ሕግ የማስከበር ሥራውን በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት
ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅራችን ከሰላም ወዳዱ
ሕዝባችን ጋር ኾኖ እየሠራ በሚገኝበት ወቅት እንዲህ አይነት
ሕገወጥ ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ኾነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ
ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እየገለጸ
በዚህ ድርጊት ላይ በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት
ላይ እንዲሁም በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን
ለማደናቀፍ በሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን
የሕግ የማስከበር እርምጃ የሚወስድ መኾኑን ያሳውቃል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
ግንቦት 13/ 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር

Source: Link to the Post

Leave a Reply