በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ ሊካሄድ ነው

በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ እንደሚካሄድ አስታወቀ ፡፡

“የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሁላችንም ሀላፊነት ነው::” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሰኞ የንቅናቄ ዘመቻ የውይይት መድረክ ይካሄዳል፡፡

የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከል ስራ ለማነቃቃትና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከጥር 1 እሰከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም የንቅናቄ ዘመቻ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ሀገርና ክልል ስርጭቱ እየጨመረ፣በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ ወደ ፅኑ ህሙማን የሚገቡ የኮሮቫይረስ ህሙማን ከፍ እያለ ቢመጣም ማህበረሰቡ ስለበሽታው የሚያደርገውን ጥንቃቄ ለማነቃቃት ዘመቻው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በአንዳንድ ሀገራት በመከሰቱ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበትም ነው ያሉት፡፡

በክልሉ እስካሁን 6ሺህ 558 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ፤ የ119 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በአሁኑ ወቅትም 113 ሰዎች ወደ ፅኑ ህሙማን ገብተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

በክልሉ በሶስት ወረዳዎች የተጀመረው የጤና መድህን በአሁኑ ወቅት 175 ወረዳዎች መድረሱን የገለጹት ሃላፊው፣ አገልግሎቱ አላስፈላጊ የህክምና ወጭን ያስቀራል ብለዋል፡፡

የቀሩትን 8 ከተማና ወረዳዎች ለማዳርስ የተጠቃሚ አባላት ወደ 80 በመቶ ለማድረስ የንቅናቄ ስራ ይሰራል ተበሏል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ ሊካሄድ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply