You are currently viewing በአማራ ክልል የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ በአሸባሪው ትሕነግ ስር ባሉ በ3 ወረዳዎች ለሚገኙ ወገኖች አፋጣኝ የጤና አገልግሎትና የወረርሽኝ ቁጥጥር እና አሰሳ እንዲደረግላቸው…

በአማራ ክልል የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ በአሸባሪው ትሕነግ ስር ባሉ በ3 ወረዳዎች ለሚገኙ ወገኖች አፋጣኝ የጤና አገልግሎትና የወረርሽኝ ቁጥጥር እና አሰሳ እንዲደረግላቸው…

በአማራ ክልል የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ በአሸባሪው ትሕነግ ስር ባሉ በ3 ወረዳዎች ለሚገኙ ወገኖች አፋጣኝ የጤና አገልግሎትና የወረርሽኝ ቁጥጥር እና አሰሳ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ ለተለያዩ ተቋማት ደብዳቤ ጽፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቁጥር 9/ጤ/1593/14 እና በቀን 9/9/2014 የተጻፈው ደብዳቤ ለአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ለአብክመ ጤና ቢሮ እንዲደርስ የሚጠይቅ ነው። የደብዳቤው ይዘት የሚከተለው ነው:_ ጉደዩ:_ አለም አቀፍ ሰብአዊ ጤና አገልግሎት እዲሰጠን ስለመጠየቅ በዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር የሚተዳደሩ ሶስት ወረዳዎች (አበርገሌ፣ጻግጅ እና ዝቅዋላ) እስከ አሁን ድረስ በጽንፈኛ ሀይል ቁጥጥር ውስጥ በመሆናቸው ምክንያት ህዝባችን በከፍተኛ ርሃብ ፥ እርዛት እና ድርቅ ከመጠቃቱም በላይ በአሁኑ ሰዓት በተለይ በአበርገሌ ወረዳ ከፍተኛ ደረጃ ሊባል በሚችል ሁኔታ የእብድ ውሻ በሽታ፣ ወባ እና ከፍተኛ የምግብ እጥረት ፣ከፍተኛ ተቅማጥና ትውከት ምልክቶች የሚያሳይ ገዳይ ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክንያት እስካሁን ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የተረጋገጠ ሪፖርት ለመምሪያችን ደርሷል። ስለሆነም ይሄንን ተከትሎ የባለሙያ እገዛ ለመስጠት እና የህክምና ምላሽ ለመስጠት አካባቢዎቹ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ቁጥር ስር የወደቁ በመሆናቸው ምክንያት ህዝቡን መታደግ አልተቻለም። በመሆኑም በእናንተ በኩል ከአለማቀፍ ድንበር የለሽ የህክምና ሰጭ ተቋማት ጋር በመነገር ለህዝቡ አፋጣኝ የጤና አገልግሎት እና የወረርሽኝ አሰሳ እና ቁጥጥር እንዲሁም የጤና አገልግሎት እንድንሰጥ ስንል እንጠይቃለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply