በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደገለፁት ÷ ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ዘመኑ ሳይጠናቅ ትምህርት መዘጋቱን አስታውሰዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት ደግሞ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ህዳር ወር ሊሰጥ የነበረው ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሰሜን ወሎ ዞን ዋግኸምራ፣ ሰሜን ጎንደር ፣ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ውስን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበርም ገልፀዋል፡፡

አሁን በክልሉ ሰላም በመፈጠሩ የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ከትናንት ጀምሮ ተከፍተዋልም ነው ያሉት፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply