በአማራ ክልል ያለው የኤች አይ ቪ ኤድስ የስርጭት ምጣኔ ከአገር አቀፍ ምጣኔ እንደሚበልጥ ተገለጸ

👉🏿 ጦርነቱ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽዖ አድርጓል

ዓርብ ግንቦት 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ያለው የኤች አይ ቪ ኤድስ የስርጭት ምጣኔ 1 ነጥብ 9 በመቶ ሲሆን፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ 0 ነጥብ 9 ነው ተባለ።

የክልሉ ስርጭት ከአገር አቀፉ የሚልቅ ሲሆን በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ኤድስ ክትትል እና ግምገማ ባለሙያ መንግሥቱ መንገሻ እንደገለጹት 175 ሺህ 955 ወገኖች በኤች አይ ቪ ኤድስ የተያዙ ሲሆን፤ ባለፉት ዓመታት የተፈጠሩ ግጭቶች እና መፈናቀሎች የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እንዲስፋፋ አድርጓል።

እንዲሁም በግጭት ወቅት አስገድዶ መደፈር እና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች እንደሚኖሩ የተናገሩት ባለሙያው እንዲህ ዓይነት ሂደቶች ስርጭቱ እንዲሰፋ እያደረጉ መኾኑን ገልጸው በግጭት ምክንያት ያቀዱት አልሳካ ሲል እና ሕይዎት አስቸጋሪ ስትኾን ሰዎች ተስፋ እንደሚቆርጡ እና በግጭት ምክንያት በሚኖረው መፈናቀል እና የኑሮ ደረጃ መቀነስ ላልተፈለገ ሥራ እንደሚያጋልጥም አንስተዋል።

እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች እያመጡት ያለው ለውጥ አዝጋሚ እና ዝቅተኛ በመሆናቸው አሁንም እንደ አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ወገኖች መኖራቸው እና በአፍላ የወጣትነት እድሜ ያሉ እና ሠርተው ራሳቸውን እና ሀገራቸውን የሚለውጡ ወገኖች ሰለባ እየኾኑ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply