በአማራ ክልል ጦርነት እየተካሄደባቸው ባሉ ዞኖች ትምህርት መቋረጡ ተገለጸ

https://gdb.voanews.com/2FECBF19-297A-4261-9A84-565338793F7A_w800_h450.jpg

በአማራ ክልል ጦርነት እየተካሄደባቸው ባሉ አራት ዞኖች ውስጥ በመማር ላይ የነበሩ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምሕርት መቋረጡን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። 

የአማራ ክልል ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀውና እራሱን የትግራይ ኃይሎች እያለ የሚጠራው አካል ወረራ ፈፅሞባቸው ባሏቸው አካባቢዎች ከ1 ሺሕ 500 በላይ ትምሕርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉና በከፊል ማውደሙን ገልፀዋል።

ህወሓት ከውድመት ጋር በተያያዘ የሚቀርብበትን ክስ አይቀበልም። 

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply