በአማራ ክልል 80 ሺ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ላይ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሳሳቢው የአንበጣ መንጋ…

በአማራ ክልል 80 ሺ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ላይ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሳሳቢው የአንበጣ መንጋ ስጋት በኢትዮጵያና በአካባቢው አገራት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የአንበጣ መንጋው በክልሉ 4 ዞኖች፣ 18 ወረዳዎች በ136 ቀበሌዎች መከሰቱን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በአጠቃላይ 328 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መውረሩን የተናገሩት አቶ ተስፋሁን ግማሽ የሚሆነውን መሬት የአውሮፕላን ርጭትን ጨምሮ በተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎች የመከላከል ሥራ ተሠርቶበታል ሲሉ ይናገራሉ። የአንበጣ መንጋው 87 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል የሚሉት አቶ ተስፋሁን፣ ከእነዚህም መካከል 30 ሺህ 500 ሄክታር የሚሆነው የሰብል ምርት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው ባደረሰው ከፍተኛ ውድመት የተጎዱ አርሶ አደሮችን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ድጋፍ ለማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል። ቢቢሲ አማርኛ ያናገራቸው የአቶ ሐሰን ባለቤት ያዩትን ማመን አልቻሉም። ያ በየዓመቱ እየተጫነ ጓዳና ጎተራቸውን ሲያጨናንቅ የነበረው ግዙፉ ማሳቸው ራቁቱን ቀርቷል። “ባለቤቴ የወደመውን ሰብል ስትመለከት ራሷን ሳተችብኝ፣ ልጆቼን ምን ላበላቸው ነው ብላ ተጨነቀችብኝ፣ ቤታችን በሰፊው የተለመደበት ስለነበር አሁን ባዶ ማሳ ስታይ ነገ ምን ልንሆን ነው ብላ ራሷን ሳተችብኝ፣ ስለዚህ አንበጣ መከላከሉን ትቼ እርሷን ሳጽናና ዋልኩ። እርሷን በሕይወት ማትረፌ ራሱ ትልቅ ደሰታ ተሰምቶኛል” በማለት ባለቤታቸው የወደመውን ሰብል ሲመለከቱ የተሰማቸውን ስሜት ያብራራሉ። አሁን ከሁለተኛው ማሳቸው የተወሰነ ነገር ለማትረፍ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ቢሆንም እንዲሁ ዝም ብሎ ላለማስበላት እንጂ ተስፋቸው ተሟጥጧል። ቀጣይ ዝናብ ጥሎ በበልግ ለማምረት፣ ካልሆነ ደግሞ መንግሥት የሚሰጠው ነገር ካለ እርሱን የሕይወት ማቆያ ለማድረግ ተስፋ ሰንቀዋል። በዛሬው እለት ጥቅምት 2013 ዓ.ም በራያ ቆቦ ወረዳ ብሮቢት በአዲስአለም፣ ብአቧሬ በዲቢና በገደመዩ ከፍተኛ የሆነ የበረሀ አንበጣ ተከስቷል። የወረዳው አመራር፣የአካባቢው ማህበረሰብ የቆቦ ጊራና አመራሮችና ሰራተኞች፣ወጣቶች፣ባለህብቶች የፀጥታ አካላት የፌደራል፣የዞንና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በቦታው በመገኘት በኬሚካልና በባህላዊ መንገድ የመከላከል ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል። ሆኖም ግን ይህ አስከፊ የበርሀ አንበጣ እስከመጨረሻው አካባቢውን ለቆ እስኪሄድና በቀሪ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ የመከላከል ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ያለው የራያ ቆቦ ኮሚኒኬሽን ነው። የበረሃ አንበጣ ባስከተለዉ የሰብል ውድመት በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ 54 ሺህ ዜጎች ለረሃብ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ተናግረዋል። ወረዳው ካሉት 20 የገጠር ቀበሌዎች በ12 ቀበሌዎች የተከሰተው የበረሃ አንበጣ ሙሉ በሙሉ የአርሶ አደሩ ሰብል ልማት መውደሙ ተገልጿል። 9 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብል መውደሙንም ኃላፊው ጨምረው ስለመናገራቸው የአዲስ ማለዳ ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply