
በአማራ ወጣቶች ማህበር የራያ ጢነኛ ሲቪክ ማህበር አዘጋጅነት ህዝባዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ:: መጋቢት 03 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ -በውይይቱም የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ -በሀገ-ወጥ የመሬት ወረራ ጉዳዮች ላይ -በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ -በራያና አካባቢው ስላለው የፀጥታ ጉዳይ ባደረገው ህዝባዊ ውይይት የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ በመያዝ ስብሰባውን አጠናቋል። 1,የተነሱትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚመለከተውን የመንግስት አካላት ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ መፍትሄ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። 2, በከተማችን ላይ በሚደረገው ህገወጥ ድርጊቶች የሚሳተፉ ማንኛውም ማህበረሰብ ከድርጊቶቻቸው እንዲቆጠቡ እና ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙትን የምንታገል እና ለህግ አካላት አሳልፈን የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን። 3,በአማራ ክልል ብሎም በዞን እና በወረዳችን ላይ የኑሮ ውድነት እንዲኖር የሚያደርጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ከዚህ ስራቸው እንዲቆጠቡ እና መንግስትም የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍተኛ የሆነ ስራ እንዲሰራልን ስንል እናሳስባለን። 4,አሁን ባለው የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ወቅቱን ጠብቆ እየተለዋወጠ እየመጣ ያለው የፖለቲካ አሰላለፍ ከግምት ውስጥ በማስገባት የክልላችን መንግስት የአማራን ሞት ለማስቆም እና የአማራን ጥቅም ለማስከበር ከሚያደርገው ትግል ጎን መቆማችንን እናሳውቃለን። 5, የአማራ ህዝብ የተጋረጠብትን የህልውና አደጋ ይቀለብስ ዘንድ ፋኖነት የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታን የዋጀ ብቸኛው የትግል መስመራችን ነው። ስለሆነም ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ቡድን በፋኖ ስም ወንጀል ሲፈፅም ቢገኝ ፋኖነትን እና ፋኖን ለጠላት አጋልጦ ቢሰጥ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን። 6,በማንኛውም ቦታ የሚገኝ የአማራ ህዝብ ወቅቱ ከፈጠረብን የህልውና አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን እና አደረጃጀታችንን አጠናክረን የምንታገልበት ጊዜ መሆኑን እናሳስባለን። 7,በማንኛውም ቦታ ያላችሁ የአማራ ወጣቶች ማህበር አደረጃጀት ከመቸውም ጊዜ በላይ ማህበራችሁን በማንቀሳቀስ ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም መከበር ከፍተኛ ትግል እንድታደርጉ ስንል እናሳስባለን። 8,ከራያ እስ ወልቃይት፣ከመተአል እስከ ደራ ሸዋ ያለው አማራ እንዲሁም ከአማራ ክልል ውጭ በአማራነታቸው የሚገደሉ እና የሚፈናቀሉ ቤታቸው የሚፈርስባቸውን ለማስቆም የክልሉ መንግስት በአፅኖት ይዞ እንዲሰራበት እያሳሰብን እኛም በዚህ ጉዳይ ከጎኑ የምንቆም መሆናችንን እንገልፃለን። የአማራ ወጣቶች የራያ ጢነኛ ሲቪክ ማህበር “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post