You are currently viewing በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የዘሩትን እህል እየገለበጡ ስንዴ እንዲዘሩ በመንግስት መታዘዙ በበርካታ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያስነሳ ነው፤ ለከፍተኛ ኪሳራም ይዳርገናል በሚል ስጋት ላይ መውደቃ…

በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የዘሩትን እህል እየገለበጡ ስንዴ እንዲዘሩ በመንግስት መታዘዙ በበርካታ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያስነሳ ነው፤ ለከፍተኛ ኪሳራም ይዳርገናል በሚል ስጋት ላይ መውደቃ…

በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የዘሩትን እህል እየገለበጡ ስንዴ እንዲዘሩ በመንግስት መታዘዙ በበርካታ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያስነሳ ነው፤ ለከፍተኛ ኪሳራም ይዳርገናል በሚል ስጋት ላይ መውደቃቸው ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ስንዴ የማያበቅሉ አካባቢዎችን ጨምሮ ማለትም ደጋማ ስፍራዎች ሁሉ እየተመነጠሩ ስንዴ እንዲዘሩ በመንግስት መታዘዙ አርሶ አደሩን ለከፍተኛ ተቃውሞ እየዳረገው ነው። አርሶ አደሩን ከአስገዳጁ ስርዓት ጋር የለየለት ግጭት ውስጥ እንዲገባ እያደረገው መሆኑ ተገልጧል። እንደ አብነትም በምስራቅ ጎጃም ቢቸና፣ምዕራብ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር እንዲሁም አንዳንድ የሸዋ አካባቢዎች ከማሳመን ይልቅ አስገዳጅነት የተከተለው የመንግስት አካሄድ ለከፍተኛ ኪሳራ ይዳርገናል በሚል ቅሬታ እየተነሳ ነው። እንደ ድንች፣ገብስ፣በቆሎ፣ጤፍ የመሳሰሉትን አስቀድመው ዘርተው የነበረ ቢሆንም እነዚህን እህሎችን በመገልበጥ ስንዴ እንዲዘሩ መደረጉ አርሶ አደሮችን የበለጠ ኪሳራ ውስጥ የሚጥል መሆኑ ተመላክቷል። አርሶ አደሮቹ እንደ አብነት ሲገልጹም በአንድ ሄክታር 60 ኩንታል ገብስ ማምረት የሚችል መሬት ተገልብጦ ስንዴ ሲዘራ ግን 15 ኩንታል እንኳን እንደማይወጣው እናውቃለን ይላሉ። ስርዓቱ መሬታቸውን እንደሚነጥቃቸው በመግለፅ ስንዴ እንዲዘሩት በተደጋጋሚ ቢያስጠነቅቃቸውም አርሶ አደሮች ለኪሳራ ይዳርገናል በሚል ፈቃደኛ እየሆኑ አይደለም። ዳሩ ግን በአንድ አንድ አካባቢዎች ማሳቸውን በኃይል እንዲገለብጡ የተደረጉ አርሶ አደሮች መኖራቸው ተገልጧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ስንዴ ወደ ውጭ እንልካለን” ማለቱን ተከትሎ አርሶ አደሩ በጉልበት የስንዴ ፖለቲካ ማስፈፀሚያ እየተደረገ መሆኑ ሁኔታውን እጅግ አሳዛኝ አደርጎታል ተብሏል። በስንዴ ፖለቲካው ምክንያት የአርሶ አደሮቹ ማሳ ሁሉ በአስገዳጅነት እየተገለበጠ እንዲዘራ ለማድረግ መሞከሩ የተፈለገው የእህል መጠን ሳይመረት ቀርቶ በቀጣይ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የለየለት ርሃብ እንዳይከሰት ያሰጋናል ሲሉም ገልፀዋል። ዘገባው የጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply