You are currently viewing በአማራ ጠልነት ስትራቴጅያዊ ግቦቻቸው የሚስማሙ የፖለቲካ ኃይሎች መላውን የአማራ ክልል የጥፋት ቀጠና ለማድረግ የግብር ወዳጃቸው ከሆነው የአማራ ብናልጽግና ጋር በመሆን በአማራ ላይ እስር፣ አ…

በአማራ ጠልነት ስትራቴጅያዊ ግቦቻቸው የሚስማሙ የፖለቲካ ኃይሎች መላውን የአማራ ክልል የጥፋት ቀጠና ለማድረግ የግብር ወዳጃቸው ከሆነው የአማራ ብናልጽግና ጋር በመሆን በአማራ ላይ እስር፣ አ…

በአማራ ጠልነት ስትራቴጅያዊ ግቦቻቸው የሚስማሙ የፖለቲካ ኃይሎች መላውን የአማራ ክልል የጥፋት ቀጠና ለማድረግ የግብር ወዳጃቸው ከሆነው የአማራ ብናልጽግና ጋር በመሆን በአማራ ላይ እስር፣ አፈና፣ ወከባ እና ማስፈራራት ከመፈጸም ጎን ለጎን በወለጋ ዋነኛ አማራን የማጥፋት ፕሮጀክታቸውን እየተገበሩ መሆኑን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ:- የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በምዕራብ ወለጋ በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል መሪር ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለፀ ጉዳዩን አስመልክቶ ተከታዩን መግለጫ አውጥቷል። የአማራን ህዝብ በሀገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ህዝብ መብቱ ተከብሮ እንዳይኖር ወይም ተቅበዝባዥ ሆኖ እንዲኖር የሚፈልጉ የፖለቲካ ኃይሎች መዋቅራዊ የዘር ፍጅት ወንጀል ካወጁበት ቆይቷል። ይህ ህዝብ በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት ግዜ ውስጥ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አስከፊ የሚባለውን እልቂት እና መፈናቀል አስተናግዷል። እያስተናገደም ይገኛል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ከወጣ በኋላ ያለ የአስተማማኝ የመከላከያ ቀጠና (Buffer Zone) ገዥ መሬቶች ተለቀው የአማራ ክልል ለወራሪ ሰራዊት እንዲጋለጥ በማድረግ በሶስቱ ክፍለ ግዛቶች ( በሸዋ፣ ወሎ እና ጎንደር) በህዝቡ እና በንብረቱ ላይ ከባድ እልቂት እንዲፈፀምበት ሆኗል። ዛሬም ድረስ ራያ፣ አበርገሌ፣ ጠለምት እና አዳርቃይን ጨምሮ በርካታ የአማራ ግዛቶች በወያኔ ጦር ቁጥጥር ስር ናቸው። በስልጣን በተኳረፉ ነገር ግን በአማራ ጠልነት ስትራቴጅያዊ ግቦቻቸው የሚስማሙ የፖለቲካ ኃይሎች መላውን የአማራ ክልል የጥፋት ቀጠና ለማድረግ ባላቸው ጉጉት የተነሳ የግብር ወዳጃቸው የሆነውን የአማራ ብናልፅግና በመጠቀም በ”ህግ ማስከበር” ስም በፋኖወች፣ በማህበረሰብ አንቂወች፣ በፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና በጋዜጠኞች ላይ የማሰር፣ የማሳደድ፣ የማፈን እና የማስፈራረት ተግባር ፈፀመዋል። በተለይም እነኝህን አካላት በማፈን እና ህዝቡን ያለ ድምፅ እና ተከላካይ በማስቀረት በክልሉ ውስጥ ያለውን ህዝብ በተለየ ሁኔታ ደግሞ በጦርነቱ በቀጥታ ያልተወረረውን የጎጃም አካባቢ የጦር ቀጠና ለማድረግ ጥረት አድርገዋል። ከሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶች በተጨማሪ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አመራር እና አባላት የዚህ ዘመቻ ዒላማ የተደረጉበት ምክንያትም ከላይ ከተጠቀሰው ዓላማ የመነጨ እንደሆነ እንገነዘባለን። ከዚህ ጎን ለጎን ዋነኛው የፕሮጀክቱ ተግባር የቀጠለ ሲሆን በተለይም የአማራ ማህበረሰብ በብዛት በሚኖርበት የወለጋ አካባቢ ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃን አማራወች በማንነታቸው ምክንያት ተጨፍጭፈዋል እየተጨፈጨፉም ይገኛሉ። በመሆኑም በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነንም ቢሆን የአማራ ህዝብ ራሱን ከእልቂት ለማዳን የሚያደርገውን ተጋድሎ ከማስተባበር ወደ ኋላ የማንል መሆኑን እያረጋገጥን ተከታዩን ጥሪ እናቀርባለን። 1/ ለመላው ኢትዮጵያውያን:_ ዛሬ በአማራ ህዝብ ላይ የተጀመረው የማሳደድ ፣ የማሰር፣ የመዝረፍ እና ዘርን የማጥፋት ዘመቻ በሁሉም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ላይም የሚቀጥል አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተገንዝበው ከግፉዓን የአማራ ህዝብ ጎን በመቆም ሁሉን አቀፍ ትግል እንዲያደርጉ፣ 2/ ለመላው የአማራ ህዝብ:_ የተጀመረው የእልቂት ዘመቻ በድንገት የተከሰተ ሳይሆን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ ቅርፅ ያለው ከጀርባው ኢትዮጵያን ከአማራ ህዝብ መብት እና ጥቅም በተቃራኒ እንደገና የመስራት ወይም የማጥፋት ዓላማ ያለው መሆኑን ተገንዝቦ ራስን እና ሀገርን የማዳን የተቀናጀ ትግል እንዲያደርግ፤ 3/ የአማራ ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ የዲያስፖራው ማህበረሰብ:_ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) እስካሁን ለሚያደርጉት ሁሉን አቀፍ ተጋድሎ ታላቅ አክሮት ያለው መሆኑን እየገለፀ አማራን እየገደለ እና እያስገደለ ያለው ስርዓት የህወሃትን ጥፋት በይዘትም፣ በቅርፅም፣ በጥልቀትም አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ያገናዘበ ትግል እንድታደርጉ፤ በሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች ክፍለ-ዓለማት ያሉ ጠንካራ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር ወጥነት ባለው መንገድ የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል። በተለይም በዲፕሎማሲው ረገድ የአማራ ህዝብ እልቂት የፀጥታው ምክር ቤት አጀንዳ እንዲሆን እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በገዥው ኃይል ላይ የጥፋቱን ደረጃ የሚመጥን እርምጃ እንዲወስድ ያለመታከት እንድትሰሩ፣ 4/ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ:_ በኦሮሞ ህዝብ ስም ስልጣን ላይ ያሉ የኦሮሞ ብልፅግና እና ስልጣን ለመያዝ የቋመጡ የኦነግ እና የኦፌኮ ልሂቃን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፃሚ፣ አስፈፃሚ እና አቀነባባሪ በመሆን ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ የሚተርፍ ታሪካዋ እዳ እያሸከሙት መሆኑን አውቆ እንዲታገላቸው፤ 5/ ለአማራ ብልፅግና:_ መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ አደረኩ የሚልባቸው የፋኖ አደረጃጀቶች በሙሉ አመራር ያላቸው እና የፖለቲካ ጥያቄም ያላቸው በመሆኑ የተጀመረው ዘመቻ ተቋርጦ ከእነኝህ የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት እንዲጀመር፣ ጥያቄው ፖለቲካዊ ምላሽ እንዲያገኝ እና የፋኖ አደረጃጀቶች ወለጋን ጨምሮ ችግር ባለባቸው ሁሉም አካባቢዎች ተሰማርተው የህዝባቸውን ህልዉና የሚጠብቁበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ እንዲሁም እስካሁን በተደረገው ዘመቻ ያለአግባብ በየማጎሪያ ካምፖች እና እስርቤቶች የገቡ ንፁሃን ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ እናቀርባለን። በመጨረሻም በዘር ማጥፋት ወንጀሉ ሰለባ በሆኑ የወለጋ አማራዎች እልቂት ምክንያት ሀዘን ላይ ላለው የአማራ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባሕርዳር-ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply