በአማሮ ወረዳና በምዕራብ ጉጂ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች መካከል እየተካሄደ በነበረ የእርቀ ሰላም ስብሰባ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን በከፈተው ተኩስ አንድ የብልፅግና አመራርን ጨምሮ የብዙ ሰ…

በአማሮ ወረዳና በምዕራብ ጉጂ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች መካከል እየተካሄደ በነበረ የእርቀ ሰላም ስብሰባ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን በከፈተው ተኩስ አንድ የብልፅግና አመራርን ጨምሮ የብዙ ሰ…

በአማሮ ወረዳና በምዕራብ ጉጂ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች መካከል እየተካሄደ በነበረ የእርቀ ሰላም ስብሰባ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን በከፈተው ተኩስ አንድ የብልፅግና አመራርን ጨምሮ የብዙ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማሮ ወረዳ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች መካከል ሠላማዊ ስብሰባ እየተካሄደ በነበረበት ቦታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡዱን በከፈተው ተኮስ የብዙ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጧል።በርከት ያሉ ሰዎችም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። አመራር ፣አርሶ አደሮች ፣የፖሊስ አባላትና ሠላማዊ ዜጎች ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት ጥቃቱ ስለመፈፀሙ ተገልጧል። እስከ አሁን ከ6 በላይ ሠላማዊ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በጫካ ውስጥ የተበታተኑና ያልተገኙም ስለመኖራቸው ተጠቁሟል፤ በመሆኑም ቁጥራቸው ከዚህም ሊበልጥ ይችላል ነው ያለው አማሮ ወረዳ ኮምኒኬሽን። በጥቃቱ ከተገደሉት መካከልም የልዩ ወረዳው የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና አንድ ፖሊስ አባል እንደሚገኙበት የዓይን እማኞች ስለመግለጻቸው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘግቧል። የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪው ደግሞ ቆስለዉ አርባ ምንጭ ሆስፒታል እንደገቡ ተሰምቷል። በተደጋጋሚ በኦነግ ሸኔና በአጋሮቹ በኮሬ አርሶ አደር ፣ነጋዴዎችና በሠላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ከመቶ በላይ ሰዎች ሞተዋል። ብዙ ቀበሌዎች ውድመዋል። ምንጭ_አማሮ ወረዳ ኮምኒኬሽን ገፅ ፎቶ:ማህበራዊ ሚዲያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply