በአሜሪካ ምክርቤት ለደረሰው ሁከት የአለም መሪዎች አስተያየት

https://gdb.voanews.com/4483C66D-1076-4C66-B426-D174C2EF72E1_w800_h450.jpg

እሮብ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በተፈፀመውና ቢያንስ ለአራት ሰዎች መሞትና ለበርካቶች መታሰር ምክንያት በሆነው ሁከት የአለም መሪዎች ድንጋጤያቸውን እየገለፁ ነው። ሁከቱ የተፈጠረው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ህዳር ወር ላይ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ምርጫ ያሸነፉትን ጆ ባይደንን ተቃውመው ወደ ምክር ቤቱ ባመሩበት ወቅት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድቤቶች ትራምፕ ምርጫ ተጭበርብሯል ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply