በአሜሪካ በተከሰተው ቅዝቃዜ ከ 60 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡በአሜሪካ የተከሰተዉ ከባድ ቅዝቃዜ እና በረዶ ነዋሪዎችን ከተሸከርካሪዎቻቸዉ ዉስጥ አላንቀሳቅስም ማለቱ ተሰማቷል፡፡የተከሰተ…

በአሜሪካ በተከሰተው ቅዝቃዜ ከ 60 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡

በአሜሪካ የተከሰተዉ ከባድ ቅዝቃዜ እና በረዶ ነዋሪዎችን ከተሸከርካሪዎቻቸዉ ዉስጥ አላንቀሳቅስም ማለቱ ተሰማቷል፡፡

የተከሰተዉ ከባድ ቅዝቃዜ እና በረዶ በሰሜን አሜሪካ ዉስጥ ከባድ ችግር ማስከተሉ ነዉ የተነገረዉ፡፡

በተፈጠረዉ ከባድ ቅዝቃዜ የተነሳ ከ 60 በላይ ሰዎች መሞታቸዉን የከተሞቹ ባለስልጣናት እየገለጹ ነው፡፡

የአገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት እጅግ ከባድ ነዉ በተባለዉ በዚህ ቅዝቃዜ ምክንያት ተሽከርካሪዎቻቸዉ በበረዶ በመያዛቸዉ የተነሳ ከሁለት ቀናት በላይ ሰዎች መኪኖቻዉ ዉስጥ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ‹‹በዚህ የገና ወቅት ወዳጆቻችሁን ላጣችሁ በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ፣ ልቤ ከእናንተ ጋር ነዉ›› ሲሉ በቲውተር ገጻቸዉ ላይ አስፍረዋል፡፡

ከካናዳ እስከ ሜክሲኮ ድንበር ድረስ ሀይሉን አበርትቶ የቀጠለዉ ይህ ከባድ ቅዝቃዜ እና በረዶ ከ60 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

እነዚህን ሰዎች ለማዳን የሚላኩ የተለያዩ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች መድረስ አልቻሉም፤ አልያም እራሳቸዉ በበረዶዉ ተይዘዉ ቀርተዋል ሲሉ ባለስልጣናቱ የሁኔታዉን ክብደት እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

በረዶዎቹ መቅለጥ ሲጀምሩ እና በበረዶዉ የተያዙ መኪኖች መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ብዙ የጉዳቱ ሰለባዎችን ማግኘት እንደሚቻል እየተነገረ ነው፡፡

በበረዶዉ የተነሳ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ወደ 250ሺህ ቤቶች እና የቢዝነስ ተቋማት የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠባቸዉ እና እስካሁን መብራት ማግኘት አለመቻላቸዉን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply