በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት 94 ሺህ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት 94 ሺህ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 94 ሺህ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም ከሰሞኑ ከተመዘገቡት ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ሃሙስም 91 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የተነገረ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ሚሊየን መድረሱንም የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

አንዳንድ ግዛቶችም ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ጋር ተያይዞ ለምርጫና ለድጋፍ ለሚወጡ ዜጎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በመስጠት የሙቀት መጠናቸውን ሲለኩ ነበር፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎችም ከቫይረሱ ስጋት ጋር ተያይዞ ትላልቅ ዝግጅቶች ከአዳራሽ ውጭ እየተደረጉ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

The post በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት 94 ሺህ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply