በአሜሪካ ባሊቲሞር ግዛት ትልቁ ድልድይ በመርከብ ከተመታ በኃለ መደርመሱ ተገለፀ፡፡በባልቲሞር ከተማ ወደብ ትልቁ ድልድይ በትልቅ መርከብ ከተመታ በኃላ 20 የሚጠጉ የነፍስ አድን ሰራተኞች ተሰ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/co91HPvZe9GKlFfY5fOEgB8-hrEl74wKiWG8OBF-koZtmsuw0BW9oV2RG_niXZe8DDfuSxpPpwLyCUdenaPnHCdxEYwc53Ys8-0CPmv_WB5BI7Ge_JUNHWcndv-YVb_5UpvzuqwLSNOUbU-2-xBd1NOHWMrg0o5lH3M4DEDAnrgbjtQC-lSgMdzuUyI8XBgmqVpszEAD6-ob9Hr_mz9RzuM3ywnLEjOvu-yphVwnwMRSGtrzByl8xOOOK_t2n96mIauWwCPWpvb4_9Tififl0bpkKPuchLGDqEVNWsyTwVv8tZ-IHOh-ie23yCXwLUvQEC66TyOMsVejSD9pdcNVlg.jpg

በአሜሪካ ባሊቲሞር ግዛት ትልቁ ድልድይ በመርከብ ከተመታ በኃለ መደርመሱ ተገለፀ፡፡

በባልቲሞር ከተማ ወደብ ትልቁ ድልድይ በትልቅ መርከብ ከተመታ በኃላ 20 የሚጠጉ የነፍስ አድን ሰራተኞች ተሰማርተዋል፡፡

በትልቁ ወንዝ ውስጥ ወድቀዋል የተባሉ ተሸከርካሪዎችን እየተፈለጉ ይገኛል ሲል የእሳት አደጋ መከላከል ቃል አቀባይ ለሲ ኤን ኤን ተናግረዋል፡፡
የ1.6 ማይል ርዝመት ያለው ባለ አራት መስመር ድልድይ በመርከቧ ከተመታ በኃላ መድርመሱ ተገልፃል፡፡

ድልድዩ በፓታፕስኮ ወንዝ ላይ የተዘረጋ ሲሆን የባልቲሞር ወደብ ውጪያኛው መሻገሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለት የተደረመሰው የባልቲሞር ወደብ ባለፈው ዓመት ከ80 ሚሊዮን ቶን በላይ ዓለም አቀፍ ጭነት ማስተናገዱ ይገለፃል፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply