በአሜሪካ እግር ኳስ ፍጻሜ ካንሳስ ሲቲ ቺፍስ ዋንጫውን አነሳ

https://gdb.voanews.com/e384fa5a-9acd-4975-a509-e1b0459ce6aa_w800_h450.jpg

በአሜሪካ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ፍጻሜ ትናንት እሁድ ተካሂዶ የካንሳስ ሲቲ ቺፍስ ቡድን የፊላደልፊያውን ኢግልስ 38 ለ35 በሆነ ውጤት አሸንፎ ዋንጫውን ወስዷል።

የቺፍሱ ቡድን መሪ፣ “ኳርተር ባክ” ይሉታል፣ የወረወራቸው ሶስት ኳሶች ለግብ በመብቃታቸው የምርጥ ተጨዋች ማዕረጉን ጭኗል።

የአሜሪካው እግር ኳስ (እነርሱ የሚጫወቱት በእጅ ነው)፣ እጅግ ተወዳጅና ፍጻሜውም በጉጉት የሚጠበቅ ነው። በረፍት ሰዓት የሚቀርበው ተዕይንትና ለቴሌቭዥን ተመልካቾች የሚተላለፈው ማስታወቂያ ከፍተኛ ትኩረትን የሚስብና ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሁኖ የሚሰነብት ነው።

በረፍት ሰዓት በሪያና የቀረበው የሙዚቃ ትርኢት ደማቅና በዓይነቱ ለየት ያለ ነበር።

ካንሳስ ሲቲ ቺፍስ የቻምፒየኑን ዋንጫ ሲያነሱ በአራት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply