በአሜሪካ የኑክሌር ማስወንጨፊያ በግለሰብ ቤት ውስጥ ተገኘ፡፡የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ግዛት ፖሊስ ከአንድ ግለሰብ ቤት የአሮጌ እቃዎች ማከማቻ ጋራዥ ውስጥ የተገኘው የዛገ ሮኬት የኑክሌር ሚሳኤ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/vhwRpgk0Nm5K7tkIqPj8XEwiaASTC2Py4WGhlzna1hfZKo1jojl8O7Uq5O_oYCiAX_-o1TPvYZcB_QyBE4XQLWB4qKBjim1YR7dxzltNlTVdIFsVTzvSXfoFQhWVc1LCGTuoY5aFJttGsDP09dRPWvbIN5R76SKxXXLAy5HX6qaXhM3KecXC3g7wSwnPyVS4xzsHqFZIw3gKARRaOzi2RfswpeivqhPBrETPYUO5Rm9W7yCyhYG_xKZUhEYwSasjHKQ29I1t6HxdXUE3sAzcjnH9ED25FfHQA3JTiNnFhWxYh1JRtfrmqES-cdf8pOR0is8o_p_GfgeSDAsSMRCH9A.jpg

በአሜሪካ የኑክሌር ማስወንጨፊያ በግለሰብ ቤት ውስጥ ተገኘ፡፡

የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ግዛት ፖሊስ ከአንድ ግለሰብ ቤት የአሮጌ እቃዎች ማከማቻ ጋራዥ ውስጥ የተገኘው የዛገ ሮኬት የኑክሌር ሚሳኤል መሆኑን ይፋ አድርጓል።

በኦሃዮ ግዛት ቤልቩ ከተማ የሚገኝ ወታደራዊ ሙዚየም አንድ እምብዛም ያልተለመደ ስጦታ እንደተበረከተለት በመግለጽ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጉን ተከትሎ ነው ጉዳዩ ይፋ የሆነው።

ይህ እንደ ጦር ቅርስነት በስጦታ እንዲቀመጥ ሙዚየሙ እንዲወስደው የጠየቁት ግለሰብ ጥያቄ ግራ መጋባትን በመፍጠሩ፣ ፖሊስ ሪፖርቱ ከደረሰው በኋላ ቦምብ አምካኝ ቡድን ወደ ግለሰቡ ቤት መላኩን የቢቢሲ ዘገባ ያስረዳል

የተገኘው ቁስ “1.5 ኪሎ ቶን የኑክሌር አረር መሸከም የሚችል ከአየር ላይ የሚተኮስ ሮኬት” መሆኑን በዝርዝር አመልክቷል። በአሁኑ ወቅት ግን በሮኬቱ ውስጥ ሊተኮስ የሚችል የኑክሌር አረር ስለሌለበት ጉዳት እንደማያደርስ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply