በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አደረገ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ በሁሉም ስቴቶች ከሚገኙ ከ500 ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በዙም በተካሄደው ውይይት በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣታት ውይይታቸውን ማጠናቀቃቸውን በዋሽንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ አስታውቋል።

በዚህም ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጫፍ የረገጠ የአገር ክህደት ጥቃት እና በማይካድራ እና በሌሎች አካባቢዎች በግፍ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።

መንግስት ተገዶ የገባበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያደርግዉን ጥረት እንደሚደግፉም አሳውቀዋል።

ለመከላከያ ሰራዊት የሞራል እና የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እንደሚገልፁም ተናግረዋል፡፡

የጁንታውን ቡድን ተላላኪዎቹ የሀሰት ወሬ ዘመቻ ለማጋለጥ እና ትክክለኛውን የቡድኑን ማንነት ለዓለም ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ፣ ለወዳጅ ሀገሮች መንግስታት እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ለማሳወቅ በተደራጀ መንገድ ለመስራት ወስነዋል።

ቡድኑ በሀገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ስም የሚያካሂደውን የፖለቲካ ንግድ በማውገዝ፣ የትግራይ ህዝብ ከመላው ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህት ጋር ሆኖ ይህን ቡድን እንዲታገል ጥሪ እቅርበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ እና የህግ አስፈፃሚ አካላት፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እና ሌሎች መንግስትታ ሁኔታውን በሚገባ አውቀው ቡድኑን ወደ ህግ በማቅረብ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ እንደዜጋ የተቀናጀ እና የተናበበ ሰራ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

The post በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply