ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች የሞት ሽረት ትግል እያደረጉበት ባሉበት የጆርጂያ የምክር ቤት ምርጫ ራፋኤል ዋርኖክ ድል ቀንቷቸዋል እየተባለ ነው፡፡ቆጠራው መቶ በመቶ ባይጠናቀቅም ከ98 ከመቶ በላይ ድምጽ ተቆጥሮ ራፋኤል ዋርኖክ አሸንፈዋል እየተባለ ነው የሚገኘው፡፡
ይህ መረጃ ከተረጋገጠም ራፋኤል ዋርኖክ ቀድሞ የባሪያ አሳዳሪ ከነበረችው የጆርጂያ ግዛት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ግዛቷን የሚወክል የመጀመሪያው ጥቁር የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ ተብሏል፡፡ዋርኖክ አሸናፊ የተባሉት የቀድሞዋን ሴት አባል ኬሊ ሊዮፋለርን በትንሽ ልዩነት በልጠው ነው፡፡
ምርጫው በድጋሚ እየተደረገ ያለ ሲሆን በድጋሚ እንዲካሄድ የተወሰነው ባለፈው ህዳር እጩዎቹ 50 ከመቶ የመራጭ ድምፅ ባለማግኘታቸው ነው ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል፡፡
***********************************************************
ቀን 30/04/2013
አሀዱ ራዲዮ 94.3
Source: Link to the Post