በአምሓ ደስታ መታሰቢያ_እንጦጦ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የኦሮሚያ ክልል ባንዴራ እንዳይሰቀል እንቅፋት ሆናችኋል በሚል የታሰሩ መምህራን ብዛት 16 ደርሷል፤ ፍ/ቤት ቀርበው ለተሃሳስ 4 ተ…

በአምሓ ደስታ መታሰቢያ_እንጦጦ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የኦሮሚያ ክልል ባንዴራ እንዳይሰቀል እንቅፋት ሆናችኋል በሚል የታሰሩ መምህራን ብዛት 16 ደርሷል፤ ፍ/ቤት ቀርበው ለተሃሳስ 4 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአምሓ ደስታ መታሰቢያ_እንጦጦ አምባ ት/ቤት ከህዳር 26/2015 ከጠዋት ጀምሮ የታሰሩ መምህራን ብዛት 16 ደርሷል። ህዳር 27/2015 በአራዳ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው ለታህሳስ 4/2015 እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጧቸዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ምንጮች እንደገለጹት ከአምሓ ደስታ መታሰቢያ_እንጦጦ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተወስደው በእስር ላይ ከሚገኙት መካከል:_ 1) መዲ ተስፋዬ፣ 2) ሰይፈ ታረቀኝ፣ 3) ጫኔ፣ 4) ታያቸው አከለ፣ 5) ፍቅሩ ግሩም፣ 6) ዘይነባ አያሌው፣ 7) ዘውዱ አረጋኸኝ፣ 😎 ማቲያስ መለሰ፣ 9) ነጻነት ውዱ፣ 10) ሄኖክ አበበ፣ 11) ገረመው ፈይሳ፣ 12) ሰራዊት፣ 13) ሀይማኖት እና 14) ገድል የተባሉ እንደሚገኙበት ተገልጧል። አምሓ ደስታ መታሰቢያ ት/ቤት በ1942 በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የልጅ ልጃቸው በአማሓ ደስታ ስም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የተቋቋመ ት/ቤት መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply