በአምስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 በአምስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ:: የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ነው እቃዎቹ የተያዙት፡፡ በዚህም ከሀምሌ እስከ ህዳር ባሉት አምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው ከ1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የወጪና የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በአምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊዬን 116 ሚሊዬን 298 ሺህ የሆነ ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድን ለመያዝ ታቅዶ ግምታዊ ዋጋቸው 1ቢሊዬን 356 ሚሊዮን 118ሺህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ተችሏል፡፡

እነዚህ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በመያዝ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጉምሩክ ኬላ እና መቆጣጠርያ ጣቢያ ሠራተኞች እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሀይሎችና ጥቆማ በመስጠት ለተባበሩ አካላት ሁሉ የገቢዎች ሚኒስቴር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በቀጣይ ወራትም ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተጠናከረና የተቀናጀ ስራ ይሰራሉ ብሏል ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ድረ ገፁ ባሰፈረው መረጃ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply