
በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በአማራ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ አራት መተላለፊያዎች ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እየደረሰ እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ገለጸ። ከ63,800 ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ እና ከ4,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የጤና፣ የመጠለያ፣ የትምህርት፣ የውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ትግራይ መድረሳቸውንም የኦቻ መግለጫ ያትታል።
Source: Link to the Post