በአራት መቶ የመንግሰት እና የግል ጤና ተቋማት በተደረገ የኤች አይቪ ስርጭት ቅኝት አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተመላከተ፡፡

የጤና ሚኒሰቴር በበላይነት ሲቆጣጠር በቆየዉ የኤች አይ ቪ ስርጭት ቅኝት በከፍተኛ ሁኔታ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን በተደረገዉ አዉደ ጥናት ተገልጿል፡፡ቅኝቱን ሲመራ የነበረዉ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት በአራት መቶ የግል እና የመንግሰት የጤና ተቋማት ላይ ነዉ፡፡

እንደ ሀገር የኤች አይ ቪ የስርጭት መጠን 0 ነጥብ 9 በመቶ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም እንደ ጋምቤላ እና አዲስ አበባ ባሉ አንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታየዉ ምጣኔ አንድ በመቶ እንደሆነ ያመለክታል፡፡በቅኝቱ የስርጭት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይባቸዉ አካባቢዎች መለየታቸዉን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪ ፕሮግራም አስተባባሪ ወይዘሮ ምርቴ ጌታቸዉ ገልጸዋል፡፡

ሴተኛ ኣደሪዎች፣ ትዳር የፈቱ፣ የትዳር አጋሮቻቸው የሞቱባቸው፣ የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፤ ወጣ ባሉ አካባቢዎች የኮንስትራክሽን ስራዎች በሚሰሩባቸዉ ስፍራዎች አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች የተለዩባቸዉ መሆናቸዉን በቅኝቱ ታውቋል፡፡የተገኘዉን የቅኝት ዉጤትም መሰረት በማድረግ  በፌደራል እና በክልል ደረጃ ምላሽ እንዲሰጥባቸዉ አቅጣጫ መቀመጡን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ቀን 26/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply