You are currently viewing በአርበኛ ዘመነ ካሴ የቀረበው ክስ ተነቧል፤ በጠበቆች በኩልም ክሱ ውድቅ እንዲወድቅ ተጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ ሸዋ…

በአርበኛ ዘመነ ካሴ የቀረበው ክስ ተነቧል፤ በጠበቆች በኩልም ክሱ ውድቅ እንዲወድቅ ተጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ…

በአርበኛ ዘመነ ካሴ የቀረበው ክስ ተነቧል፤ በጠበቆች በኩልም ክሱ ውድቅ እንዲወድቅ ተጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አርበኛ ዘመነ ካሴ ህዳር 12/2015 በባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቧል። ጉዳዩን የተመለከተው ችሎቱም በዐቃቢ ህግ የቀረበበትን ክስ አንብቦ አስደምጧል። የአርበኛ ዘመነ ካሴ ጠበቆችም በክሱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለፍርድ ቤቱ በዝርዝር አስመዝግበዋል። ጠበቃ ህሩይ ባዩ እንደገለጸው የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲሆን በጠበቆች በኩል ተጠይቋል። አርበኛ ዘመነ ካሴም ስለ ችሎቱ ሂደት በአጠቃላይ በቃልም በጽሑፍም አቤቱታውን አሰምቷል። ዐ/ህግ በቀረበው የክስ መቃወሚያ እና አቤቱታ ላይ መልሱን እንዲያቀርብ ለዛሬ 9:00 ተቀጥሯል። አርበኛ ዘመነ ካሴ ለፍርድ ቤት ያቀረበው በእጅ ጽሑፉ ያቀረበው አቤቱታም አብሮ ተጋርቷል። በእጅ ጽሁፍ ካቀረበው አቤቱታ መካከል:_ በብዙ ሽህ ሀሚቆጠሩ ደጋፊዎቼ እና ቤተሰቦቸ በችሎቱ ተገኝተው እንዳይከታተሉ እየተደረገ ዛሬ ላይ ደርሰናል የሚለው ይገኝበታል። ባ/ዳር ከተማ የውጊያ ግንባር እስኪመስል ድረስ ከፍ/ቤት ቀጠሮ ዋዜማ ጀምሮ በምድር እና በሰማይ ከዲሽቃ እስከ ክላሽ በታጠቁ ኃይሎች እየተወረረ መሆኑን የገለጸበት ይገኝበታል። እኔ ዘመነ በድንግል ማርያም ልጅ መንፈስ የምመራ፣ ሰውን በሙሉ የማፈቅር ንጹህ እንጅ አንድ የክፉ ጥግ ያበቀለኝ ወንበዴ አይደለሁም፤ ይህንም ሊያጠፉኝ ሌት ተቀን ተግተው የሚሰሩት ያውቁታል ሲልም ገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply