You are currently viewing በአርበኛ ዘመነ ካሴ የክስ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ ሸዋ አርበ…

በአርበኛ ዘመነ ካሴ የክስ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አርበ…

በአርበኛ ዘመነ ካሴ የክስ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አርበኛ ዘመነ ካሴ ህዳር 12/2015 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በድጋሜ በባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለህዳር 16/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። ህዳር 12/2015 ጠዋት በነበረው ችሎት ለአርበኛ ዘመነ ካሴ ክሱ የተነበበለት ሲሆን ጠበቆችም የክስ መቃወሚያ ማቅረባቸውን ተከትሎ ዐቃቢ ህግ መልስ እንዲሰጥ በሚል ነበር ድጋሜ ለከሰዓት የተቀጠረው። ከተለያዩ አቅጣጫዎች አርበኛ ዘመነ ካሴ እና በህግ ማስከበር ስም በእስር ላይ የሚገኙ ፋኖዎች፣የአማራ ልዩ ኃይል አባላትና ሌሎች ፍትህ ፈላጊ ወገኖችም እንዲፈቱ እየተጠየቀ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply