በአሰላ አካባቢ አንድ ተቋም በሚያካሂደዉ የአህያ ቄራ በቀን ቢያንስ ከ200 እስከ 300 የሚሆኑ አህያዎች ለእርድ እንደሚቀርቡ ተገልፀ። የቻይና ኩባንያ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስዶ በመቋቋም…

በአሰላ አካባቢ አንድ ተቋም በሚያካሂደዉ የአህያ ቄራ በቀን ቢያንስ ከ200 እስከ 300 የሚሆኑ አህያዎች ለእርድ እንደሚቀርቡ ተገልፀ።

የቻይና ኩባንያ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስዶ በመቋቋም አህያን በማረድ ቆዳዉን የመላክ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገልፃል።

ይህንን ያሳወቀዉ ብሩክ ኢትዮጵያ የተሰኘ በእንስሳት በተለይም በጋማ ከብት ላይ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነዉ።

ብሩክ ኢትዮጵያ ከመንግስት ጋር በተደጋጊሚ ይህ ነገር እንዲቆም የዉትወታ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም፣ መንግስት ወንድ አህዮችና የታመሙ፣የደከሙ አህያዎች ናቸዉ ለእርድ የሚቀርቡት የሚል ምላሽ የሰጣቸዉ ቢሆንም መሬት ላይ ያለዉ እዉነት ግን እሱ እንዳልሆነም ተገልፃል።

ድርጅቱ በዛሬዉ ዕለት ባካሄደዉ ወርኽሾፕ ላይ እንዳስታወቀዉ በሀገራችን ያሉ የጋማ ከብቶች በተለይም አህያ ላይ ከባድ አደጋ መጋረጡን አስታዉቋል።

በሀገራችን ከዚህ ቀደም ሁለት የአህያ ቄራዎች ማለትም በቢሾፍቱ እና አሰላ የነበሩ ሲሆን ከተዘጉ በኃላ የአሰላዉ ዳግም መከፈቱን ነዉ ድርጅቱ ያስታወቀዉ።

የአህያ ቆዳ ንግድ በዚህ ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ መበራከቱን የሚገልፁት የብሩክ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ዩሐንስ ቃሲም በተለይም በቻይና ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቱ የተነሳ ንግዱ በአፍሪካ ሀገራት ተበራክቷል ብለዋል።

ከቆዳዉ የሚገኘዉን ንጥረነገር ወይም ኬሚካል ለተለያዩ ህክምና የማዋል ልምድ ያላት ቻይና በከፍተኛ ሁኔታ የቆዳዉ ፈላጊ በመሆናቸዉ ሀገራችንን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የአህያ ቆዳ ላይ አደጋ ጋርጠዋል ብለዋል።

የአህያ ቆዳ እ.ኤ.አ በ2001 በኪሎ ከነበረበት 20 ሚሊዮን ዶላር በአሁን ሰዓት ማለትም ጥናቱ እስከ ተካሄደበት 2017/18 ወደ 820 የአሜሪካ ዶላር እንደገባም ተገልፃል።

ይህንን የአህያ ቆዳ ንግድ ያካሂዱ የነበሩ የአፍሪካ ሀገራት እንደ ኬንያ፣ሴኔጋል፣ቦትስዋና፣ታንዛኒያ የመሳሰሉ ሀገራት ቄራዉን የዘጉ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ዳግም የአሰላዉን ቄራ መከፈቷን ዳይሬክተሩ አቶ ዩሐንስ ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት ቄራዉ ስጋዉን መላክ በግዚያዊነት ያቆመ ቢሆንም ቆዳዎችን እየላከ እንደሚገኝና ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም የተወሰኑ የአህያ ስጋ ቤትች መኖራቸዉም ተገልፃል።

በአሰላ የሚገኘዉ የአህያ ቄራ በመንግስት እዉቅና ያለዉ በመንግስት የሚጠበቅ ጭምር መሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።

ኬንያ ከዚህ በፊት አራት የአህያ ቄራ የነበራት ሲሆን በዜጎቿ በገጠማት ተቃዉሞ አራቱንም ቄራዎች መዝግቷ ነዉ የተነገረዉ።

የብሩክ ኢትዮጵያዉ ዳይሬክተር እንዳስታወቁት በሀገራችን የሚወጡ ህጎችና ደንቦች የእንስሳተን መብትና ደህንነት የሚጠብቁ መሆን አለባቸዉ ብለዋል ።

በሀገራችን 13.3 ሚሊዮን የሚጠጉ የጋማ ከብቶች ያሉ ሲሆን 8ሚሊዮን የሚጠጉት አህያዎች መሆናቸዉ ተገልፃ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ የአህያዎች ቁጥርን አደጋ ዉስጥ ይኸተዋል ተብሏል።

ብሩክ ኢትዮጵያ በ2008 ዓ.ም ላይ የተቋቋመ በእንስሳት መብትና ጥበቃ ላይ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ተቋም ሲሆን በተለይም በአማራ፣ኦሮሚያ እና በቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሲሰራ የቆየ ተቋም መሆኑም ተገልፃል።

በአቤል ደጀኔ

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply