You are currently viewing በአስለቃሽ ጭስ የታጠነው፣ በደም የረሰረሰ ውሏችን…! በዮሐንስ ዘኆኅተ * …  ከአቤት ሆስፒታል ባጣራነው መሠረት 16 ሰው ተጎድቶ የገባ ሲሆን አንዱ ሕይወቱ አልፏል። እንደተለመደው የ…

በአስለቃሽ ጭስ የታጠነው፣ በደም የረሰረሰ ውሏችን…! በዮሐንስ ዘኆኅተ * … ከአቤት ሆስፒታል ባጣራነው መሠረት 16 ሰው ተጎድቶ የገባ ሲሆን አንዱ ሕይወቱ አልፏል። እንደተለመደው የ…

በአስለቃሽ ጭስ የታጠነው፣ በደም የረሰረሰ ውሏችን…! በዮሐንስ ዘኆኅተ * … ከአቤት ሆስፒታል ባጣራነው መሠረት 16 ሰው ተጎድቶ የገባ ሲሆን አንዱ ሕይወቱ አልፏል። እንደተለመደው የዓድዋን በዓል ለማክበር ጠዋት ላይ ነጭ ልብሳችንን ለብሰን በላዩ ነጠላ ጥለንበት ከወንድሜ ከተመስገን ጋር ነበር ከቤት የወጣነው። ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ መንገድ ላይ ያገኘን ከጊዮርጊስ አቅጣጫ የሚመጣው ሰው ሁሉ አፍንጮ በር ጋር ዘግተውታል አትልፉ ተመለሱ እያለ ይነግረን ነበር። እኛም ግድ የለም አይተን እንመለሳለን ትንሽ ቆይተው ይከፍቱታል በማለት ተስፋ አድርገን መንገዳችንን ቀጠልን። እንደተባለው በአፍንጮ በር በኩል ፤ በሰሜን ሆቴል በኩል ወደ ጊዮርጊስ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው። በዮሐንስ በኩል እንይና እንመለሳለን ብለን ስንሔድ በዚያም በኩል በፖሊሶች ተዘግቷል። እንሳለም ብለን ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ገብተን ለደቂቃዎች ከቆየን በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ በአፍኣ መጮህ ሲጀምር ከግቢው ስንወጣ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ሕዝቡ እንዳይሄድ አግደውት የነበሩ ፖሊሶች ሕዝቡ እንዲሔድ በመፈቀዱ እንደሆነ ተረዳን። እኛም ከሌሎች ጋር ተሰብስበን እየዘመርን መሔድ ጀመርን። በግምት ከመቶ ሜትር በኋላ ሌሎች ፖሊሶች ከዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፒያሳ የሚወስደው መንገድ ላይ ዘግተው ቆመዋል። ሕዝቡ እየዘመረ አጠገባቸው ሲደርስ በዱላ መማታት ጀመሩ። ሕዝቡ ሲበታተን ግማሹ ሲወድቅ አንዱ በአንዱ ላይ እየወደቀ ብዙ ሰው ተጎድቷል። መሐል ላይ ጥይት መተኮስ ተጀመረ። [እኔ የሰማሁት ሁለት ጊዜ] በዚህ ጊዜ ወንድሜ ተመስገን ወድቆ ተነሳ። እኔ አደናቅፎት መስሎኝ ነበር ላካንስ በጥይት ተመትቶ ነበር። ደሙ በነጩ ሱሪው ላይ መውረድ ጀመረ። ይዘነው ወደ አናንያ ሆስፒታል በመቀጠልም በሪፈራል ወደ አቤት ሆስፒታል ወሰድነው። አቤት ሆስፒታል ባጣራነው መሠረት 16 ሰው ተጎድቶ የገባ ሲሆን አንዱ ሕይወቱ አልፏል። በጥይት የተመታ፣ በሰደፍ ጀርባው ተመትቶ አጥንቱ የወለቀ፣ እጁ በዱላ ተመትቶ አጥንቱ የተሰበረ ….. ሌላም ሌላም ሞልቷል። እንግዲህ ምን እንላለን? ሀገር አለን’ን? ትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነኝ #FailedState ዮሐንስ ዘኆኅተ

Source: Link to the Post

Leave a Reply