በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ተገለጸ

 
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መሰረት 23 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ፣ የጠቅላይ መምሪያ ዕዝ አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)  በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት መገምገሙን አስታውሰዋል፡፡
የፀጥታ ችግር በተከሰተባቸው የአማራ ከልል አካባቢዎች፣ የተቋማት እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑንም ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply