በአሶሳው ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ቀብር ተፈጸሟል:: (አሻራ ሚዲያ ሐምሌ 2/2014 ዓ.ም) ሰሜን አሜሪካ በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ በተፈጠረ ብሄር ተኮር ግድያ ትናንት ሐሙስ 3 ሰዓት ላይ…

በአሶሳው ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ቀብር ተፈጸሟል:: (አሻራ ሚዲያ ሐምሌ 2/2014 ዓ.ም) ሰሜን አሜሪካ በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ በተፈጠረ ብሄር ተኮር ግድያ ትናንት ሐሙስ 3 ሰዓት ላይ ግድያና ጭፈጨፋና መፈፀሙንና በዚህም ጉዳት መድረሱን መዘገቡ ይታወሳል። በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ አምባ ደሱ የተባለ የ40 ዓመት ጎልማሳ፣ መዲና ሁሴን የተባለች የ30 ዓመት ወጣት እንዲሁም ቢላል አህመድ የተባለ የአምስት አመት ህፃን የሚገኙበት ሲሆን መዲናና ቢላል እናትና ልጅ ናቸው። ሟቾችንም ሆነ ቁስለኞችን ወደቤተሰብና ወደከፍተኛ የህክምና ተቋም ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን ትናንት አርብ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል። የወረዳው አመራር ለሟቾችም ሆነ ለተጎጂዎቹ ምንም አይነት ድጋፍ አለማድረጉ የተገለፀ ሲሆን በንፁሃኑ ሞት የወረዳው አመራር እጅ አለበት ተብሎ እንደሚታመን ተነግሯል። በዚህ ጥቃት ከማህበረሰቡም ሆነ ከአመራሩ በኩል ምንም ጉዳት የደረሰባቸዉ እንደሌለ የገለፁት ምንጮቻችን ሟቾች በንግድ ስራ ይተዳደሩ እንደነበርም አስረድተዋልደ አሁንም በወረዳው ወስጥ ያሉት አማራዎች በስጋት እየኖሩ ስለመሆናቸውም ተመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply