በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚገለገሉ ነዋሪዎች፣ የእናቶች የወሊድ ክትትል አገልግሎትን ጨምሮ በሆስፒታሉ ተገቢውን ህክምና ለማግኘት ከፍተኛ ችግር መኖሩን ገልጸዋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚገለገሉ ነዋሪዎች፣ የእናቶች የወሊድ ክትትል አገልግሎትን ጨምሮ በሆስፒታሉ ተገቢውን ህክምና ለማግኘት ከፍተኛ ችግር መኖሩን ገልጸዋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሰራተኞች በሰዓት አለመገኘት፣ የቀጠሮ ብዛት፣ የመድኃኒት እጥረት፣ የመብራት እና በቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የሽንት ቤት ችግር በምክንያትነት ጠቅሰዋል። በተቻለ መጠን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት በሆስፒታሉ የእናቶች ክትትልና ድጋፍ ባለሙያ ሲስተር አመለወርቅ ዋልታው፤ የተገልጋይ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የባለሙያ ቁጥር አለመኖሩን ጠቁመው ቸግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ከማለዲን አልፈኪ በበኩላቸው በተለይም አሁን ወቅቱ ክረምቱ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመብራት መቆራረጥ በስፋት የሚስተዋል በመሆኑ የእናቶችንና የጨቅላ ህጻናትን ህይወት ለመታደግ እንኳን መቸገራቸውን ተናግረው፣ በጄኔሬተር የመተካት አማራጩም በነዳጅ ችግር ምክንያት ውጤታማ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሌላው በስፋት የተነሳው ችግር የመድኃኒት እጥረት ሲሆን፥ ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ኢቢሳ ከሚባል የመድሃኒት አከፋፋይ ድርጅት መድኃኒት ይገዛ እንደነበር ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ከአሶሳ አዲስ-አበባ በሚወስደው መንገድ የጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጧል ብለዋል፡፡ መድኃኒት በጨረታ ለመግዛት ድርጅቶችን አወዳድሮ እንደነበር አስታውሰው፣ በመንገድ ችግሩ ምክንያት ሆስፒታሉ ያስያዘው ከ100 እስከ 200 ሺህ ብር መክሰሩንም ገልጸዋል፡፡ በዚህም ህብረተሰቡ በሆስፒታል ደረጃ 25 ብር የሚገዛውን መድኃኒት ከውጭ ከ300 እስከ 500 ብር ለመግዛት እየተገደደ እንደሆነ ጠቁመዋል ሲል የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል ያለው ኢትዮ መረጃ ኒውስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply