በአሶሳ ከተማ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ እስር እና ወከባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ! ባህርዳር:- መጋቢት 13/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በቤንሻንጉል ጉም…

በአሶሳ ከተማ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ እስር እና ወከባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ! ባህርዳር:- መጋቢት 13/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ከተማ በአማራ ተወላጆች ላይ እስር እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገልጿል። ከ06/07/2014 ዓ.ም ጀምሮ መታወቂያ እየተቀበሉ ወደ ፓሊስ ጣቢያ በመውሰድ ድብደባ እና ወከባ መፈፀሙን ምንጫችን ተናግረዋል። ይህ ድርጊት አሁንምእየተባባሰ ስለመጣ የሚደርስልን አካል የለም ብለዋል። ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት የአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አጎራባች ዞንና ወረዳዎች የተውጣጡ አካላት በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው የሚል ማስተባበያ ተዘግቧል ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply