በአሶሳ ከተማ በሶስት ቀናት ውስጥ ከ552 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ የትምባሆ ምርቶች ተያዙ

በአሶሳ ከተማ በሶስት ቀናት ውስጥ ከ552 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ የትምባሆ ምርቶች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሶሳ ከተማ በሶስት ቀናት ውስጥ ከ552 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ የተለያዩ የትምባሆ ምርቶች መያዛቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ የደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ተቆጣጣሪዎች ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ተቆጣጣሪዎች እና ከከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባሎች ጋር በመቀናጀት ነው ከታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ትንባሆ ምርቶቹ የተያዙት፡፡
በዚህም ከ552 ሺህ 750 ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ የተለያዩ የትምባሆ ምርቶችን መያዝ መቻሉን ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአሶሳ ከተማ በሶስት ቀናት ውስጥ ከ552 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ የትምባሆ ምርቶች ተያዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply