You are currently viewing በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ በልማት ላይ ተሰማርተው የሚኖሩ አማራዎችን ልዩ ልዩ የፍረጃ ስሞችን በመስጠት በፖሊስ እና በሚሊሾች ማሰሩ እና ማሳደዱ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ በልማት ላይ ተሰማርተው የሚኖሩ አማራዎችን ልዩ ልዩ የፍረጃ ስሞችን በመስጠት በፖሊስ እና በሚሊሾች ማሰሩ እና ማሳደዱ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ በልማት ላይ ተሰማርተው የሚኖሩ አማራዎችን ልዩ ልዩ የፍረጃ ስሞችን በመስጠት በፖሊስ እና በሚሊሾች ማሰሩ እና ማሳደዱ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ደን ተጨፍጭፏል፣ ፋኖ ናችሁ፣ ህገ ወጥ ናችሁ በሚል ሽፋን አማራውን ከሚያለማው እና ከሚኖርበት ቀዬ ጭምር እንዲሳደድ እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል። በቤንሻንጉል ክልል “ምን እንደሆነ አላወቅንም መጀመሪያ ህገወጥ ነው፤ ፋኖ መጥቷል እየተባለ ሰዉ እየተሰበሰበ እየታሰረ፣ ንብረቱ እየተዘረፈ ነው ያለ” ይላሉ በአሶሳ ዞን የባምባሲ ከተማ ነዋሪ። “ይታሰራል፤ ያለህ በፕሌን ቆርጠህ ትሄዳለህ፤ የሌለው ወደ ኦሮሚያ ይሄዳል፤ እነዛ ሰዎች ይድረሱ አይድረሱ አይታወቅም” በማንነታቸው አማራ የሆኑ አርሶ አደሮች ከመጋቢት 20/2014 ጀምሮ ከክልልም አለ ይባላል፤ በባምባሲ ወረዳ ፖሊሶች እና ሚሊሾች በየገጠሩ የእርሻ ማሳቸው ባሉበት እየታደኑ እንዲታሰሩ ይደጋል ተብሏል። የአማራ አልሚዎችን ለማፈናቀል “ደን ተጨፈጨፈ” የሚል ሽፋንን በመጠቀም በአካባቢው ከ7 ዓመት በላይ በህጋዊ መልኩ ለመንግስት ግብር እየከፈሉ እና እያለሙ የሚኖሩት ሁሉ ንብረታቸው እየተዘረፈ በጅምላ እየታፈሱ እና እየታሰሩ ነው ይላሉ የባምባሲ ነዋሪዎች። ንብረቴን ተዘርፌ ከምታሰር በሚል ስጋት አልሚዎች ከማሳቸው እየሸሹ ወደ ከተማ እየገቡ መሆኑም ተገልጧል። በአጠቃላይ በተረጋጋ መንፈስ ለማልማት አልቻልነም የሚሉት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች አልፎ አልፎ መሃል ከተማ ላይም ሆነ ከአውሮፕላን ሲወርዱ የእርሻ መሳሪያ ይዘው የሚገኙ አማራዎችም እንዲታሰሩ ይደረጋል ተብሏል። በአማራ ላይ ግፉ በዛ የሚሉት ነዋሪዎቹ የአፈሳ እስሩ የሚፈጸመው በባምባሲ ወረዳ መሆኑን ጠቁመዋል። ገንዘብ የሌለው ሆኖ የአውሮፕላን ትኬት ለመቁረጥ ያልቻለ ወርልድ ቪዥን የተባለ ድርጅት ሲሰራበት በነበረ ተቋም ላይ እንደሚታሰር ተነግሯል። በአንድ ቀን ብቻ ከ150 በላይ አማራዎች በአፈሳ እስር ተይዘው ስለማየታቸው የሚናገሩት ምንጫችን እስሩ እንደሁኔታው የሚጨምርበትና የሚቀንስበት ሁኔታ ስለመኖሩም ጠቁመዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply