በአሶሳ ግጭት በማስነሳት የተከሰሱ 32 ግለሰቦች እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ እና አካባቢዋ አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ሰኔ 2010 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ ግጭት በማስነሳት በተከሰሱ 32 ግለሰቦች ላይ ከሰባት እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
 
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ሰኔ 16፣ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የ17 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የንብረት ውድመትም ደርሷል፡፡
 
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ32 ሰዎች ላይ ክስ መስርቷል፡፡
 
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ እና አካባቢዋ አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ቀደም ሲልም በእነዚሁ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
 
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በአሶሳ ከተማ በዋለው ችሎት ደግሞ በተከሳሾቹ ላይ ከሰባት ዓመት እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
 
የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተላለፈባቸው 32 ሰዎች መካከል 15ቱ በሌሉበት ውሳኔ የተሰጠባቸው ናቸው፡፡
 
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የፍርድ ሂደቱን ከጨረሱ በኋላ ከየትኛውም ህዝባዊ መብት ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ማገዱም በውሳኔው ተመልክቷል፡፡

The post በአሶሳ ግጭት በማስነሳት የተከሰሱ 32 ግለሰቦች እስከ 21 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply