በአሸባሪው ሕወሐት ውድመትና ኪሳራ የደረሰባት የመሐል ሜዳ ከተማ ወደ ቀደመ እንቅስቃሴዋ ለመመለስ ጥረት እያደረገች ቢሆንም ጣራ በነካው የኑሮ ውድነት ሕዝቡ እየተሰቃየ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገ…

በአሸባሪው ሕወሐት ውድመትና ኪሳራ የደረሰባት የመሐል ሜዳ ከተማ ወደ ቀደመ እንቅስቃሴዋ ለመመለስ ጥረት እያደረገች ቢሆንም ጣራ በነካው የኑሮ ውድነት ሕዝቡ እየተሰቃየ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአሸባሪው ሕወሐት ውድመትና ኪሳራ የደረሰባት የመሐል ሜዳ ከተማ ወደ ቀደመ እንቅስቃሴዋ ለመመለስ ጥረት እያደረገች ቢሆንም ጣራ በነካው የኑሮ ውድነት ሕዝቡ እየተሰቃየ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት አንዳንድ የገበያ ማረጋጋት ተግባራትን እያከናወነ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በችግር ውስጥ ለሚገኙ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደ ቀይመስቀል ያሉ ረድኤት ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ ቢሆኑም የፍትሐዊነት የአመላመልና የስርጭት ችግር እንዳለ በስፋት ይነሳል። በተለይም የችግሩ ዋነኛ ገፈት ቀማሽ የሆነው የመንግስት ሰራተኛው በነበረው ችግር ያጠራቀመውን ገንዘብ አውጥቶ ልጆቹንና ቤተሰቡን ሲያሸሽ በከፍተኛ ክፍያ ቀለብ እየሸመተ ጊዜውን ያሳለፈና ደሞዝም የተከፈለው እጅግ ዘግይቶ መሆኑ ተገልጧል። ከሁሉም የበለጠ የኑሮ ውድነቱ እያንገበገበው እንደሚገኝና በድጋፍ በኩልም ሌሎች ተመሳሳይ የጦርነት ችግር ውስጥ በነበሩ አካባቢዎች እንደተደረገው አይነት ድጋፍ እንዳልተደረገለት የችግሩ ሰለባ የሆኑት የመንግስት ሰራተኞች በምሬት ተናግረዋል። ለችግራቸውም አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ፎቷ ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply