በአሸባሪው ትህነግ ግዞት ስር ላላችሁ እና በጨካኞች ለተፈናቀላችሁ ወገኖቼ !! ከሁሉ አስቀድሜ እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ!! ~~~~~~~ አሸናፊ ገናን~~~~~~~ እንደሚታወቀው ህዝባ…

በአሸባሪው ትህነግ ግዞት ስር ላላችሁ እና በጨካኞች ለተፈናቀላችሁ ወገኖቼ !! ከሁሉ አስቀድሜ እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ!! ~~~~~~~ አሸናፊ ገናን~~~~~~~ እንደሚታወቀው ህዝባችን ን በዘር፣በሃይማኖት እና በስውር ደባ ለ 45 ዓመት ሲያሰቃይ የነበረው ሃይል ዛሬም በወንድሞቻችን ላይ የማያባራ ግፍ እና የቀውስ ሰለባነት ውስጥ ይገኛሉ። በአማራ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለው ነገር እጅግ የሚያሳዝን ቢሆንም አበው “ከመሞት መሰንበት ይሉ ዘንድ ” አሁንም በግፈኞች የከበረ ጥላ ስር ለምትገኙ የወሎ አማራዎች እና በጨካኞች እኩይ ዓላማ ከኦሮሚያ እና ከተለያዩ አካባቢወች ተፈናቅላችሁ ያላችሁ ወገኖቸ እንኳን አደረሳችሁ። ሁሉም ነገር በአምላክ ፈቃድ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነውና ወገኖቼ ባላችሁበት ሁሉ ብርታቱንና ጥንካሬውን ሰጥቷችሁ እንደምታሳልፉት እምነቴ ነው። በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ ለ”ሃጣን” የመጣ ለ”ፃድቃን” እንደሚባለው በግፈኞች እና በራስ ወዳዶች የመጣውን ሃጢያት በእናንተ ላይ በመፈፀሙ ፈጣሪ በቃ ይለን ዘንድ ፈጣሪያችንን እንጠይቅ!! ቃሉ ይፈፅም ዘንድ ግድ ነውና !! “ሁሉም ነገር ለበጎ” መሆኑንም እንመን !! ወገኖቼ አድሱ ዓመት ሁላችንም #ነፃ የምንወጣበት ዘመን ይሁንልን ዘንድ ተመኘሁ። ግፈኞችንና አሸባሪዎችን እየተዋጋህ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዮ ሃይል፣የአማራ ፋኖ ፣የአማራ ሚሊሻና የአፋር ልዩ ሃይልም እንኳን ለአድሱ ዓመት አደረሳችሁ። አዲሱ ዓመት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያሸንፉበት ዘመን ይሆን ዘንድ እመኛለሁ። መስከረም 01/01/2015 ዓም ፎቶ:- ከፋይል ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply