You are currently viewing በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአቢ ደንጎሮ ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ አንድ አባት እንዲሁም ከጊዳ አያናም ሁለት በቤታቸው የነበሩ አማራዎች በግፍ መገደላቸው ተሰምቷል፤ አስከሬን ለማንሳት አልተቻለም…

በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአቢ ደንጎሮ ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ አንድ አባት እንዲሁም ከጊዳ አያናም ሁለት በቤታቸው የነበሩ አማራዎች በግፍ መገደላቸው ተሰምቷል፤ አስከሬን ለማንሳት አልተቻለም…

በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአቢ ደንጎሮ ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ አንድ አባት እንዲሁም ከጊዳ አያናም ሁለት በቤታቸው የነበሩ አማራዎች በግፍ መገደላቸው ተሰምቷል፤ አስከሬን ለማንሳት አልተቻለም ተብሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከአቢ ደንጎሮ ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ አንድ አባት እንዲሁም ከጊዳ አያናም ሁለት በቤታቸው የነበሩ አማራዎች በግፍ መገደላቸው ተሰምቷል፤ አስከሬን ለማንሳት አልተቻሉም ተነግሯል። በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ቱሉዋዩ ቀበሌ ላይ ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2014 በጠራራ ጸሀይ እና በአደባባይ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱት መገደላቸውን ምንጮች ለአሚማ ተናግረዋል። ግድያው የተፈጸመባቸው አባት አቶ ታከለ አራጌ ይባላሉ፤ ከወራት በፊት በአማራዊ ማንነታቸው ለቦትሮ ቦራ ቀበሌ ተፈናቅለው ወደ አቢ ደንጎሮ ወረዳ ቱሉዋዩ ቀበሌ ከመጡት ተጎጅዎች መካከል አንዱ ነበሩ። የሽብር ቡድኑ በግፍ የገደላቸው አቶ ታከለ በወጉ እንዳይቀበሩ እንኳ አስከሬን መደበቁ ተሰምቷል። ከላይ ከቢሮ ነው ታፍነን ያለንው፤ መስተዳድሩ ከአሸባሪው ኦነግ ጋር ነው አብሮ የሚሰራው የሚሉት ነዋሪዎቹ መውጫ እና መግቢያችን ተዘግቶ በርሃብ እየተሰቃየን እንገኛለን፤ ውሃ እንኳ እንዳንቀዳ በሽብር ቡድኑ ተቆርጦብናል፤ ወደ ወንዝ እንዳንወርድ ይገድሉናል ሲሉ ተደምጠዋል። የፌደራል መንግስት የመከላከያ ኃይል በአካባቢው በመመደብ መንገድ እንዲያስፍት፣ በረሃብ ከሚከሰት እልቂት እንዲታደጋቸው ተማጽነዋል። በተያያዘ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ከአንገር ጉትን በቅርብ ርቀት መንደር 4 አካባቢ ጥቅምት 7 ቀን 2014 ከሰዓት በኋላ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጸጋዬ በላይ እና ብርሃኑ ምትኩ የተባሉ ሁለት አማራዎችን በቤታቸው እያሉ በጥይት መግደሉ ተሰምቷል። የሟቾችን አስከሬን ለማንሳት ከከተማ አንወጣም፣ አልታዘዝንም በሚሉ የመከላከያ ሰራዊት አካላት አቋም ምክንያት ከተገደሉት ጸጋዬ በላይ የተባለ ወንድማችንን አስከሬን የአውሬ ሲሳይ ሆኗል ተብሏል። በአንጻሩ በማህበረሰቡ ትብብር የብርሃኑ ምትኩን አስከሬን አንስቶ በጉትን ሚካኤል ለመቅበር ተችሏል። በአካባቢው ባሉ በትሕነግ ቅጥረኞች ጥቆማ መገደሉን ምንጮች ተናግረዋል። መንገድ ለወራት በመዘጋቱ በርሃብ ማለቃችን ነው ድረሱልን ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply